
መጋቢት 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በፊቤላ ዘይት ማምረቻ ኢንዱስትሪና በደብሊው ኤ ዘይት ፋብሪካ በመገኘት የመስክ ጉብኝትና ከባለሀብቶች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅትም በቀን 1ሚሊዮን 500 ሽህ ሊትር ዘይት የማምረት አቅም ያለው ፊቤላ የዘይት ፋብሪካ በግብዓት አቅርቦት ችግርና በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ካለው የማምረት አቅም ከ40 በመቶ በታች እያመረተ መኾኑን የፋብሪካው ሥራ አስኪያጁ አቶ ሰለሞን ለገሰ ገልጸዋል፡፡
ፊቤላ ዘይት ፋብሪካ ሥራ ከጀመረ አንድ ዓመት ማስቆጠሩንና በዚህ ጊዜ ውስጥም ከ70 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት በማምረት ለኅብረተሰቡ እንዳሰራጨም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ የደብሊው ኤ ዘይት ፋብሪካ በግብዓት አቅርቦትና በካፒታል እጥረት ምክንያት ካለው የማምረት አቅም እስከ 30 በመቶ ብቻ እያመረተ እንደኾነ ተጠቅሷል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ሐሰን መሐመድ በፋብሪካው በአካል በመገኘታቸው የችግሮችን ጥልቀት መረዳታቸውንና ለመፍትሔውም መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
የተነሱትን የመብራት፣ የካፒታል እጥረት እና የግብዓት አቅርቦት ችግሮች በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥረት እንደሚደረግም አሰረድተዋል፡፡
አሁን እየተስተዋለ ያለውን የዘይት እጥረት ለመቅረፍ መንግሥት በልማት ድርጅቶች በቀጥታ ተገዝቶ እንዲቀርብ እያደረገ ሲኾን ከዚህ በተጨማሪም 322 ባለሀብቶች በፍራንኮ ቫሉታ ያለቀለት የምግብ ዘይት እንዲያስገቡ እየተደረገ መኾኑንና ፍትሐዊ ሥርጭት እንዲኖር እየተሠራ እንደሚገኝ አቶ ሐሰን ገልጸዋል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/