አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በምሥራቅ አማራ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት መዋቅር ላይ ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ ሃብት ማውደሙ ተገለጸ።

141

ጎንደር: መጋቢት 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት የሥራ አመራር ቦርድ አባላትና የባለ ድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በጎንደር ከተማ እየተካሔደ ነው።
በመድረኩ ተቋሙ ሥራውን ከጀመረበት ከሐምሌ 2008 ዓ.ም ጀምሮ በምዝገባ ሽፋን፣ በምዝገባ ጥራትና በምዝገባው የዜጎችን ተጠቃሚነት የነበረውን አፈፃፀም እየተገመገመ ነው።
በተለይ ከ2014 ዓ.ም ከህልውና ዘመቻው መልስ በምዕራብ አማራ የተሠሩ አንኳር ተግባራትና በምሥራቅ አማራ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ያደረሰው ውድመት ተነስቷል።
የአማራ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ኀላፊ ወይዘሪት መዓዛ በዛብህ የመንግሥት አገልግሎት በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ እንዲሆንና ለሀገር እድገት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በምሥራቅ አማራ ባደረሰው ውድመት በስምንት ዞኖች እና በ67 ወረዳዎች ባለው መዋቅር ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ማውደሙን አንስተዋል።
አሠራሮችን ዘመናዊ ለማድረግም ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የምዝገባ (ዳታቤዝ) እየለማ መሆኑን ኀላፊዋ ጠቅሰዋል።
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊና የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ገረመው ገብረ ፃዲቅ መድረኩ አደረጃጀቶችን ለማጠናከርና ደንቦችን ለማሻሻል ብሎም አሠራሮችን ለማዘመን ትልቅ ሚና እንዳለው አንስተዋል።
ኹሉም ኩነቶች ተመዝግበው የመረጃ ምንጭ ኹኖ ማየትን ራዕይ ያደረገው ተቋሙ የልደት፣ የሞት፣ ጋብቻ፣ ፍቺና የጉዲፈቻ ዋና ዋና ኩነቶችን የመመዝገብ አገልግሎት ይሰጣል።
ዘጋቢ፦ ፍፁምያለምብርሃን ገብሩ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የቻይናና ኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ትስስር ለማጠናከር ይሠራል” የቻይና ኤምባሲ
Next articleሥርዐት አልባው ንግድ እና ስጋት የፈጠረው የኑሮ ውድነት!