
መጋቢት 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ቻይና እና ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር እንደሚሠራ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን በአማራ፣ ሲዳማና ደቡብ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝተዋል።
ኤምባሲው የአምባሳደሩን ጉብኝት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የቻይናና ኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት ይከናወናሉ ብሏል።
ዘርፉን ለማጠናከር የሚከናወነው ሥራ የኹለቱን ሀገራት ተጠቃሚነት እንደሚያጎለብተውና ዘርፈ ብዙ የሥራ እድል እንደሚፈጥር አመልክቷል።
ቻይናና ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ባለሃብቶችን ከማሰማራት አንስቶ በቴክኖሎጂና ገበያ ትስስር እንዲሁም በሰው ኀይል አቅም ግንባታ የኹለትዮሽ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ ይታወቃል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/