
ሰቆጣ: መጋቢት 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)፣ የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌውና የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት ነው በሰቆጣ ከተማ ድጋፍ የተደረገው።
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እንዳሉት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራና በአፋር ሕዝብ ላይ በፈጠረው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጎጅ ለሆኑ ወገኖች ገቢዎች ሚኒስቴርና ጉምሩክ ኮሚሽን የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ ነው። እስካሁንም ለዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከ115 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብና አልባሳት ድጋፍ አድርገናል ነው ያሉት።
በአሁኑ ወቅትም በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚውል ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብና አልባሳት ድጋፍ ይዘን መጥተናል ብለዋል።
የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራና በአፋር ሕዝብ ታሪክ ይቅር የማይለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት ማድረሱን አንስተዋል። የዋግ ሕዝብ በኢትዮጵያ የረጅም ዓመታት ታሪክ ለፍትሕና እኩልነት የታገለ፣ ለተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ችግሮች የማይበገር ጽኑ ሕዝብ ነው ብለዋል። ይህ ሕዝብ ሲቸገር ድጋፍ ስናደርግ ከፍ ያለ ሐሴት ይሰማናል፤ የሕዝብን ሐብት ለሕዝብ ነው ያበረከትነው ሲሉም አጋርነታቸውን አሳይተዋል።
በቀጣይም የዋግ ሕዝብ ካጋጠመው ችግር እስኪወጣ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የዋግ ሕዝብ ያጋጠመውን ችግር በመረዳት ገቢዎች ሚኒስቴርና ጉምሩክ ኮሚሽን ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን አሁንም ድረስ በዋግ፣ በጎንደርና በራያ አካባቢ በወረራ በመያዝ ሕዝባችንን ለከፋ የምግብ እጥረትና ለረሐብ እየዳረገ ነው። የሽብር ቡድኑን የጥፋት መንገድ በማስቆም የሕዝባችንን ስቃይ በአጭር ጊዜ እናስቆማለን ብለዋል።
ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለመደገፍ መንግሥታዊና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ርብርብ እያደረጉ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ችግራቸው እስኪፈታ ድረስ ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት። ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያዎች ለሚገኙ ወገኖቻችን ኹለገብ ድጋፋችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን፤ የወራሪውን የጥፋት መንገድ እስክናስቆም ትግላችን ይቀጥላል ብለዋል።
ዘጋቢ:- ስማቸው እሸቴ – ከሰቆጣ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/