የአንጎለላና ጠራ ወረዳ ለጀግኖች ሰማእታት ቤተሰቦች እና በኅልውና ዘመቻው ተጋድሎ ለፈጸሙና ንቁ ተሳትፎ ለነበራቸው አካላት እውቅና ሰጠ፡፡

117

ደብረ ብርሃን: መጋቢት 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን የአንጎለላና ጠራ ወረዳ ለጀግኖች ሰማእታት ቤተሰቦች እና በኅልውና ዘመቻው ተጋድሎ ለፈጸሙና ንቁ ተሳትፎ ለነበራቸው አካላት እውቅና ሰጥቷል፡፡

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን የጥፋት ተልዕኮ ለማክሸፍ እና ለመደምሰስ በጦር ሜዳ በክብር ለተሰው ሰማእታት ቤተሰቦች፣ ከዘመቻ ተመላሾች እና ንቁ ተሳትፎ ለነበራቸው ነው የእውቅና እና ምሥጋና መርሃ ግብሩ የተዘጋጀው፡፡

በመርኃግብሩ ለሰማእታት ቤተሰቦች 200 ካሬ ሜትር የቤት መሥሪያ ቦታ እና የ5 ሺህ ብር ድጋፍ ተበርክቶላቸዋል፤ ቤቱን ለማሠራት ወረዳው ቃል ገብቷል።

በዘመቻው የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው 3 ሺህ ብር ተበርክቶላቸዋል፤ ከባለሃብቶች ጋር በመነጋገር ተጨማሪ ድጋፍ ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡

የወረዳው ዋና አሥተዳዳሪ አቶ ከተማ አንበርብር ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን በዘላቂነት የምንደግፍበት መንገድ ተመቻችቷል ብለዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረ ጻዲቅ ለጀግኖቹ የመስዋእትነታቸውን ትክ ማግኘት ባይቻልም እውቅና እና ምሥጋና መቸር ተገቢ መኾኑን ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡- ብርቱካን ማሞ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የማንነትና የወሰን ጥያቄ ሕጋዊ እንዲሆን እንሠራለን” የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር)
Next article“ወልቃይት ላይ እንገናኝ”