“የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የማንነትና የወሰን ጥያቄ ሕጋዊ እንዲሆን እንሠራለን” የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር)

328

ጎንደር: መጋቢት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “ወልቃይት የትግላችን መነሻ፣ የአንድነታችን ማሳያ የነፃነታችን አርማ” በሚል መሪ መልዕክት ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራን ለመጎብኘት ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተውጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር) ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር በመሆን ሽኝት አድርገውላቸዋል።

የመርሃ ግብሩ ዓላማ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራን የተፈጥሮ ፀጋ ለማወቅ፣ በሕዝቡ ላይ የደረሰውን ግፍና በደል በአካል ለመመልከት፣ የአማራን ሕዝብ የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጠናከር ነው።

በጉዞው ከ600 በላይ ከክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ናቸው ጉዞ የጀመሩት። ለተጓዦቹ ሽኝት ያደረጉት ምክትል ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር) የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ነዋሪዎች የአማራ ማንነታቸውና የወሰን ጥያቄያቸው ሕጋዊ እንዲሆን እንሠራለን፤ እናንተም ከሕዝቡ ጎን እንድትሆኑ ብለዋል።

ዘጋቢ:–በቀለ ተሾመ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበምሥራቅ በለሳ ወረዳ የመሬትን ስበት በመጠቀም ስንዴን በመስኖ የማልባት ዘዴ ውጤታማ መኾኑን አርሶ አደሮች ተናገሩ።
Next articleየአንጎለላና ጠራ ወረዳ ለጀግኖች ሰማእታት ቤተሰቦች እና በኅልውና ዘመቻው ተጋድሎ ለፈጸሙና ንቁ ተሳትፎ ለነበራቸው አካላት እውቅና ሰጠ፡፡