
ጎንደር: መጋቢት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምሥራቅ በለሳ ወረዳ ደንጎር ቀበሌ የሚገኙ ከ76 በላይ አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም 57 ሄክታር መሬት የስንዴ ልማት እያለሙ ነው። አርሶ አደሮቹ በክረምት ያለጥቅም የሚፈሰውን የዝናብ ውኃ ወደ አንድ ቦታ እንዲጠራቀም በማድረግ ነው በመስኖ የስንዴ ልማት እያለሙ የሚገኙት።
አርሶ አደሮቹ ይበልጥ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድም በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል እገዛ እያደረገላቸው ነው።
የምርምር ማዕከሉ ኀላፊ መንተስኖት ወርቁ የመስኖ ውኃው ወደ ማሳዎች እንዲዳረስ ያለምንም የኤሌክትሪክና ሌላ አማራጭ “ሲፈን ፓምፕ” በተሰኘ ቴክኖሎጅ ወይም በመሬት ስበት በመታገዝ አርሶ አደሮቹን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
የተሻሉ ምርት ሊሰጡ የሚችሉ የስንዴና ሌሎች ሰብሎች ዝርያዎችን በማቅረብና በማልማት፣ የግብዓትና የሙያ እገዛዎችን በማድረግ፣ የተሻሉ አሠራሮች እንዲስፋፉና አርሶ አደሮች ተግባራዊ እንዲያደርጉት በማድረግ በኩል ማዕከሉ የድርሻውን እየተወጣ ነው።
አስተያየታቸውን ከሰጡ የምሥራቅ በለሳ ወረዳ አርሶ አደሮች መከካል አርሶ አደር መልካሙ ዳኘውና አርሶ አደር ዘመኑ ተገኘ እንደተናገሩት የመሬትን ስበትን በመጠቀም ተግባራዊ እየሆነ የሚገኘው ስንዴን በመስኖ የማልባት ዘዴ ውጤታማ ነው። ከአሁን በፊት በነዳጅ ኀይል በሚሠራ ጀኔሬተር ታግዘው ውኃውን እየሳቡ ለመስኖ ይጠቀሙ የነበሩት አርሶ አደሮቹ በመሬት ስበት መጠቀም መቻላቸው ወጭ እንደቀነሰላቸው አስረድተዋል።
በምርት ዘመኑ በምሥራቅ በለሳ 827 ሄክታር መሬት በመስኖ እየለማ ይገኛል። ከዚህ ውስጥ 275 ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ እየለማ ነው።
በዚህም በተያዘው የመስኖ ልማት 3ሺህ 618 አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መልካሙ እንግዳው ለአሚኮ ተናግረዋል።
የጎንደር ምርምር ማዕከል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሰፋትና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሶስቱም የጎንደር ዞኖቸ ከ400 ሄክታር በላይ የመስኖ ስንዴ እየለማ ነዉ።
የማዕከሉ ኀላፊ እንደተናገሩት የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል አኩሬ አተር፣ ማሾ፣ ማሽላና ሰሊጥን በቆላማ አካባቢወች ቅመማ ቅመምን በወይና ደጋ ቦታዎች እንዲሁም የገብስ፣ ስንዴና የጥራጥሬ ሰብሎችን በደጋማ አካባቢዎች ላይ የዝርያ ማሻሻያ፣ የሰብል እንክብካቤና ጥበቃ ምርምሮችን እያካሄደ ይገኛል።
ዘጋቢ፡-ሀይሉ ማሞ -ምሥራቅ በለሳ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/