
ባሕር ዳር: መጋቢት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 11ኛ ዓመት በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች እየተከበረ ነው፡፡ በዓሉ በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች እንዲከበር በአማራ ክልል የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ጽሕፈት ቤት እቅድ አውጥቶ ሲሠራ መቆቱን የማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ተናኘ አበበ ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡
አቶ ተናኘ እንዳሉት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 11ኛ ዓመት ሲከበር በአማራ ክልል ከመጋቢት 20/2014 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 5/2014 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የቦንድ ግዥ በሕብረተሰቡ ፍላጎት እንዲከናወን እየተደረ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ባለሙያው የቦንድ ግዥው ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው ለእያንዳንዱ ዞን እና ቀበሌ በኮታ የሚቀመጥ ሳይሆን በሕዝቡ ፍላጎት ተመስርቶ የሚፈጸም እንደሆነም ነው የነገሩን፡፡ በዚህም ቦንድ ግዥውን ውጤታማ ለማድረግ የንግድ ባንክ እና ልማት ባንክ ዝግጁ ሆነው እንዲያስተናግዱ መደረጉን ነው ያስረዱት፡፡
በዓሉ በሁሉም አካባቢዎች በፓናል ውይይት እና በኪነጥበብ ሥራዎች እየተከበረ ነው ያሉት አቶ ተናኘ ሕዝቡ ግድቡ የራሱ ሀብት እንደኾነ ተረድቶ የቦንድ ግዥም ይሁን ስጦታዎች እንዲያከናውን ግንዛቤ ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ባለሙያው እንደነገሩን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በተፈጥሮ ሀብት ልማት የተሠራውን የጉልበት የገንዘብ ግምት ሳይጨምር በቦንድ ግዥ እና ልገሳ የተሰበሰበውን ገንዘብ ስንመለከት:
👉በ2011 ዓ.ም ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡
👉በ2012 ዓ.ም ከ7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡
👉2013 ዓ.ም ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡
👉2014 ዓ.ም እስከ የካቲት መጨረሻ ድረስ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል፡፡
ባለፉት 11 ዓመታት ማለትም የቦንድ ግዥ ከተጀመረ ጀምሮ በአማራ ክልል ብቻ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ባለሙያው አስረድተዋል፡፡ አቶ ተናኘ የሕዳሴ ግድብ ግንባታን ሕዝቡ ከዚህ ቀደም እንዳደረገው በቦንድ ግዥም ይሁን በሌሎች መንገዶች ግድቡ እስኪጠናቀቅ እንዲደግፉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ምሥጋናው ብርሃኔ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/