
ባሕር ዳር: መጋቢት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እና በአማራ ክልል አዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግር እልባት ለመስጠት የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ የጸጥታ አካላት በግልገል በለስ ከተማ እየመከሩ ነው።
የሁለቱ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በቀጣናው በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት በሚያስችላቸው እቅድ ላይ እየተወያዩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በአዋሳኝ ዞኖች አካባቢ እየታየ ያለውን አለመረጋጋት በዘላቂነት በመፍታት የሁለቱ ክልል ሕዝቦች የቆየ ወንድማማችነትን በማጠናከር ወደ ልማት ለማስገባት በትኩረት እንደሚሠራ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አብዮት አልቦሮ ተናግረዋል።
በውይይቱ የሕዝቦችን ሰላምና ደኅንነት በማስጠበቅ የጋራ የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የትኩረት አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እየተካሄደ ባለው የጋራ የጸጥታ ምክክር ላይ የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄኔራል ደስታ አብቼን ጨምሮ፣ የአማራ ክልል የሕዝብ ደሕንነት እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው እና ሌሎች ከፍተኛ የክልልና የዞን አመራሮች መገኘታቸውን ከመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/