
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግሥቴ በፈረንሳይ ሊዮን በኢንተርፖል ዋናው ጽሕፈት ቤት በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችና ሽብርተኝነትን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የሁለት ቀናት ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም ላይ የአውሮፓ ፖሊስ ሕብረት፣ የመካከለኛውና ምሥራቅ ሀገሮች ዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ፣ በኢንተርፖል በተለያዩ የሥራ ኃላፊነት ላይ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች በውይይቱ ተሳትፈዋል።
በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች፣ ሽብርተኝነት፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና በሰው አካል የመነገድ ወንጀል ላይ በሀገራት መካከል መከናወን ባለባቸው ጉዳዮች መረጃ መለዋወጥ፤ መከታተል፤ መቆጣጠርና ለሕግ ለማቅረብ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በኢትዮጵያ በኩልም ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግሥቴም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስን ሪፖርት አቅርበዋል።
የሕብረቱ ሀገራት እየተገናኙ ወንጀለኞችን አድኖ ለመያዝ እና መረጃ እየተለዋወጡ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ቅድመ ሁኔታዎች አስቀምጠዋል፡፡
በተያያዘም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግሥቴ ከኢንተርፖል ዋና ጸሐፊ ዩርገን ስቶክ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የኢንተርፖል ዋና ጸሐፊ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይም ሰፋ ያለ ሀሳብ ያነሱ ሲሆን ለወደፊቱም በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/