በመሠረታዊ ምርቶች ላይ የታየዉን የዋጋ ንረት ለመቀነስ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

88

አዲስ አበባ: መጋቢት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ በመሠረታዊ ፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት መከሰቱንና ይህም ከዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት ጋር የተገናኘ መሆኑን አብራርተዋል።

የዩክሬን እና የሩስያ ጦርነት በመሠረታዊ ፍጆታ ምርቶች ላይ ጭማሪ እንዲታይ ሌላው ምክንያት መኾኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡በተለይም በዘይት፣ በስንዴ እና በነዳጅ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንደታየም ነው የተናገሩት፡፡ ይህ ደግሞ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ለኑሮ ዉድነት ምክንያት መሆኑን ነው የጠቀሱት።

የገበያ ሥርዓቱ የተሳለጠ አለመኾኑ እና የኢኮኖሚ አሻጥር መብዛቱ ለዋጋ ግሽበቱ ሌላኛዉ መንስኤ እንደኾነም ዶክተር ለገሰ አንስተዋል። መንግሥትም የዋጋ ንረቱን ለመፍታት አቅዶ እየሠራ መሆኑን ነው የገለጹት። የመፍትሔ አቅጣጫ መቀመጡንም አስገንዝበዋል፡፡

ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ አሻጥሩን ለመፍታት ግብረ ኀይል ተቋቁሞ ሕጋዊ እርምጃ መዉሰድ መጀመሩን ተናግረዋል። በገበያ ላይ ያለውን የዘይት እጥረት ለመፍታት የዘይት ምርት ወደ ሀገር መግባቱን ያነሱት ዶክተር ለገሰ የተፈጸሙ ግዥዎችም በአፋጣኝ ወደ ሀገር አንዲገቡ እየተሠራ ስለመኾኑም አንስተዋል።

የዘይት አምራቾች በበቂ ሁኔታ ምርት እንዲያመርቱ ለማድረግ እየተሠራ እንደኾነም አረጋግጠዋል፡፡ በመስኖ እና በበልግ ወቅት የስንዴ ምርት ተመርቶ ለሕዝቡ እንዲደርስ እየተሠራ እንደኾነም አስረድተዋል።

በአማራ እና በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የማይገባ ጠብ ለመፍጠር የተሳሳተ ትርክትን የሚፈጥሩ አካላት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ ያሳሰቡት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ሁለቱ ሕዝቦች ባለፉት 27 ዓመታት ጭቆናን ለመጣል በጋር ሲታገሉ የቆዩ አብሮነታቸዉ የጠነከረ ሕዝቦች ናቸዉ ብለዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ በተሳሳተ ትርክት ሁለቱን ሕዝቦች ለማጋጨት የሚጥሩ ማኅበራዊ አንቂዎች ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡም አሳስበዋል። በአሸባሪዉ ኦነግ ሸኔ ላይም መንግሥት እርምጃ እየወሰደ መኾኑን ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ:–ኤልሳ ጉዑሽ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ለተጣለበት 11ኛ ዓመት የመታሰቢያ ዕለት አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
Next articleከኢንተርፖል አባል ሀገራት ጋር በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዙሪያ ውይይት ተደረገ።