“ሀገር ከቁስሏ እንድታገግምና እንድትቀጥል ወላጆች፣ መምህራን እና የእምነት ተቋማት ትውልድ ማነፅ ላይ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል” የሃይማኖት አባቶች

159

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያን ታላቅነት እና የሕዝቦቿን የቆዬ አብሮነት በማስተማር ፋንታ መለያየትን፣ ጽንፈኝነትን እና ጠባብነትን የሚሰብኩ የአመለካከት ህመምተኞችን ፈጥኖ ማከም ባለመቻሉ እንደ ሀገር ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ አማኝ ማኅበረሰብ በሚኖርባት ኢትዮጵያ አብሮነት፣ መከባበር፣ መረዳዳት፣ መተዛዘን እና አንዱ ለሌላዉ መራራት የሕዝቦቿ መገለጫ እሴቶቿ ሆነው ቆይተዋል፡፡ የእነዚህ እሴቶች እየተሸረሸረ መምጣት እንደ ሀገር እየተስተዋለ ላለዉ አለመግባባት ምክንያት ሆኗል፡፡

ብዝኃነት በነገሰባት ኢትዮጵያ የአብሮነት መስተጋብር ግድግዳ፣ ማገር እና ምሰሶ የሆኑት እሴቶች ለምን እየተሸረሸሩ መጡ ስንል የሃይማኖት አባቶችን ጠይቀናል፡፡

ወላጅ የኀላፊዎች ሁሉ ቀንዲል ነው፡፡ ልጆች የወላጆች ነጸብራቅ ናቸዉ፡፡ ቤተሰብ ደግሞ የሀገር ምሳሌ ነው፡፡ ወላጅ የሚያስተዳድራቸዉን የቤተሰብ አባላት በስርዓት ኮትኩቶ፣ ስለ ሀገር ፍቅር፣ ስለ ሰዉነት እና አብሮነት እያስተማረ ካሳደገ ሀገር የልጆች አመለካከት ዉጤት ነች የሚሉት የሃይማኖት አባቶቹ የሀገራችን የመረቀዘ ቁስል እንዲያገግም ወላጆች ቀዳሚውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

ሀገር ማለት ሰዉ ነዉ፤ የአንዱ መኖር ለሌላዉ ደግሞ ዋስትና ነው፤ በመሆኑም ይላሉ የሃይማኖት አባቶች ሁሉም በተለይ ወላጆች፣ መምህራን፣ ማኅበረሰቡ፣ የመገናኛ ብዙሃን አካላት እና መንግሥት ሀገርን የማዳን ተግባርን በኀላፊነት ወስዶ መስራት መጀመሪያ ለህሊና ቀጥሎ ለታሪክ ተጠያቂ ከመሆን ያድናል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ባለ ገናና ታሪክነቷን የስልጣኔ ምንጭ እና የሰዉ ልጅ መነሻነቷን፣ ሕዝቦቿ የአኩሪ እሴቶች ባለቤትነቷን እና የጋራ ቤትነቷን በማስገንዘብ ፋንታ መለያየትንና ጽንፈኝነትን የሚሰብኩ የአመለካከት ህመምተኞችን ኅመማቸዉ እንይዛመት ፈጥኖ መፍትሔ መሻት ይገባልም ተብሏል፡፡

ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ወንድሞቻችንን ለመቀበል ዝግጅት አጠናቀናል” የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ነዋሪዎች
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ለተጣለበት 11ኛ ዓመት የመታሰቢያ ዕለት አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።