
ሑመራ: መጋቢት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሕዝብ ትግል ፍሬ አፍርቶ ዛሬ ላይ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ሲናፍቀውና ሲመኘው የነበረውን ማንነቱን ተላብሶ፣ ነጻነቱን ተጎናፅፎ የትግል ጊዜ አጋሩን በሁሉም ቦታ ተገኝተው ስለ ከፈሉት መስዋእትነት አመሥግነዋል።
በቅርቡ ለሚካሄደው “አማራን እንወቅ” ኹለተኛ ምዕራፍ መርሐ ግብር የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የክት ልብሷን ለብሳ፣ የነጻነት ካባዋን ተጎናጽፋ እጆቿን ዘርግታ ልጆቿን ለመቀበል ዝግጁ ኾናለች።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያነጋገራቸው የሑመራ ከተማ ነዋሪዎች የወንድሞቻቸውን መምጣት በጉጉት እንደሚጠብቁት ገልጸዋል።
የሰላም ኢትዮጵያ ሆቴል ባለቤት የኾኑት ወይዘሮ ስሜነሽ ሞላ ለአሚኮ በሰጡት አስተያየት ስለ ነጻነታችን የታገሉ፣ የሕይወት መስዋእትነትን የከፈሉ ልጆቻችን ናቸውና በራችን ከፍተን ልንቀበላቸው ዝግጁ ነን ነው ያሉት።
ሌላኛው ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት ባለሃብት አድምጠው ሰረበ የታገሉላትን ምድር ለማየት በመምጣታቸው አባት ልጁን እንደሚናፍቅው እኛም በፍፁም ፍቅር ልንቀበላቸው ዝግጁ ነን ብለዋል።
ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈሉባትን ምድር ለማየት መምጣታቸው አንድነታችን የማይነጣጠልና ለጠላት የማንበገር መኾናችንን ማረጋገጫ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅት ማጠናቀቁን የሑመራ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ እና የዝግጅት ኮሚቴው አስተባባሪ አቶ ተስፋሁን አበበ ገልጸዋል።
ከመላው የአማራ ክልል ዞኖች የተውጣጡ ከ600 በላይ እንግዶች “ወልቃይት የትግላችን መነሻ፣ የአንድነታችን ማሳያ፣ የነጻነታችን ዓርማ አማራን እንወቅ ” መርሐ ግብር ላይ ተሳታፊ እንደሚኾኑና በመርሐ ግብሩም የወልቃይት ጠገዴን አማራዊ ባሕል ለማሳወቅ ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ ተስፋሁን አስታውቀዋል።
ዘጋቢ፡-ያየህ ፈንቴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/