
መጋቢት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የእስራኤል የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ለሚመጡ ጎብኚዎች የቡድን ቪዛ እገዳ መጣሉ ይታወሳል።
በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳም አባቶች እና በእስራኤል የኢፌዴሪ ኤምባሲ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከሕዝብና ኢሚግሬሽን ጉዳይ የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ከተለያዩ አካላት ጋር በተደረገው ተደጋጋሚ ምክክር ነው የቡድን ቪዛ እገዳ የተነሳው፡፡
አምባሳደር ረታ ዓለሙ የቡድን ጉዞ እገዳው እንዲነሳ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው የመንግሥት አካላት እንዲሁም የእስራኤል መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ወዳጅነት በመመልከት ውሳኔውን እንዲቀየር በማድረጉ ምሥጋና አቅርበዋል።
ውሳኔው በእየሩሳሌም የሚገኙ ቅዱሳን መካናትን ለመሳለም እና ጸሎት ለማድረግ ለሚመጡ ኹሉ መልካም በመኾኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
የእስራኤል የፓርላማ አባል ጋዲ ይባርከን “የእስራኤል አምላክ ፈቃድ ኾኖ ይህ መልካም ዜና ለኢትዮጵያዊያን በመድረሱ ደስታዬ ከፍ ያለ ነው” ብለዋል።
በእየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንባቆም “ምዕመናን ከመላው ዓለም ወደ ኢየሩሳሌም እየመጡ የሚያከብሩት በዓል በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለኹለት ዓመታት ዝግ ኾኖ ከቆየ በኋላ አሁን በመከፈቱ ደስ ብሎናል” ነው ያሉት፡፡
ብፁዕ አቡነ እንባቆም “እገዳው ተነስቶ የትንሣኤ በዓልን ለማክበር ከሚመጡት ኢትዮጵያዊያን ጋር ለመገናኘት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመኾኑ ደስታችን ታላቅ ነው”ብለዋል።
የቡድን ጉዞ እገዳው እንዲነሳ ላደረጉት ለእስራኤል መንግሥት እና ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው አካላት ኹሉ ምሥጋና አቅርበዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/