
መጋቢት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ማስተርካርድ የመንግሥት አገልግሎት የክፍያ ሥርዐትን ለማዘመን የሚያስችላቸውን ሰምምነት አድርገዋል፡፡
ስምምነቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የማስተርካርድ የክፍያ አማራጭን ከኤሌክትሮኒክ ሰርቪስ አገልግሎት ፖርታል ጋር በማቀናጀት ዜጎች ክፍያዎችን ኦንላይን እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) ጥረታችን ኢትዮጵያን ከጥሬ ገንዘብ ሕትመትና ሥርጭት ወጪ ማላቀቅና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂያችን ተግባራዊ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡
ከማስተር ካርድ ጋር የሚደረገው ትብብር ኹለገብ ዲጂታል የክፍያ መፍትሔዎችን በማቅረብ ዜጎች በማንኛውም የባንክ ካርድ ክፍያ እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል ያሉት ሚኒስትሩ፥ የገቢ አሰባሰብን ለማሻሻል እና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያግዝ መግለጻቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
የማስተር ካርድ የምሥራቅ አፍሪካ ሥራ አስኪያጅ ሸርያር አሊ ቀልጣፋ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ፈጠራ የታከለበት የዲጂታል የክፍያ አማራጮችን በመዘርጋት የኢትዮጰያ መንግሥትን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡
አገልግሎቱ በሚቀጥለው ሳምንት የሚጀመር ሲኾን ዜጎች ከውጭ ሀገራት ጭምር ባሉበት ቦታ ኾነው ለተጠቀሙት የመንግሥት አገልግሎት በማሰተር ካርድ የክፍያ አማራጭ ክፍያዎችን ኦንላይን መክፈል ይችላሉ፡፡
በመጀመሪያው ዙር የትግበራ ምዕራፍ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅት አባላት ይህንን የክፍያ መተግበሪያ አማራጭ በመጠቀም ፍቃድ ለማውጣትና ለማደስ በማንኛውም የክፍያ ካርድ ዓይነት ክፍያ መፈፀም ይጀምራሉ፡፡
ይኽንን አሠራር ለመተግበር ማስተር ካርድ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስምምነት ላይ የደረሱት በ2020 ሲኾን ይህም “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቲጂን” መሠረት በማድረግ ነው።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/