“ነዋሪዎችን ለእንግልት የሚዳርጉና የመልካም አስተዳደር ችግር የሆኑ አሠራሮችን ለማስወገድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትኩረት እየሠራ ነው” የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር

193

ባሕር ዳር: መጋቢት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በከተሞች የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አሰጣጥና አውቶሜሽን ሥርዓት ላይ ትኩረት ያደረገ የልምድ ልውውጥ አውደ ጥናት በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ባዘጋጀው አውደ ጥናት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀንን ጨምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከተማ አሥተዳድር ኅላፊዎችና ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።
መድረኩ ዜጎች ከመንግሥት የሚፈልጓቸው አገልግሎቶችን ውጤታማነት ለመገምገምና በከተሞች መካከል ያሉ መልካም ልምዶችን ለማሳየት ያለመ ነው።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉጌታ ታደሰ ከመላው ኢትዮጵያ ወደ ጎንደር የመጡ እንግዶች ጎንደር ላይ ያሉ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን እንዲገመግሙ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ዳይሬክተር ጄነራል አንዱዓለም ጤናው የትብብር መድረኩ ከተቋቋመ አስራአንድ ዓመታት በላይ ቢሆነው ባለፉት ሦስት ዓመታት የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጓል ብለዋል። በአውደ ጥናቱም የከተሞች የተቀመረ ተሞክሮ ቀርቦ ሌሎች የወል አድርገው እንዲወስዱ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀን ነዋሪዎችን ለእንግልት የሚዳርጉና የመልካም አስተዳደር ችግር የሆኑ አሠራሮችን ለማስወገድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የከተማ አስተዳድሮች የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን፣ ደረጃውን የጠበቀና ሥርዓት ባለው መንገድ የሚመራ ለማድረግ በትኩረት ይሠራል ያሉት አቶ ፈንታ ለሕዝብ ግልጽነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ቀልጣፋና ተደራሽ አሠራር እንዲኖር በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎች ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ ከተሞች ከማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አኳያ የፈፀሙት ተግባር ውይይት እየተደረገበት ነው።
ዘጋቢ፦ ፍፁምያለምብርሃን ገብሩ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበአማራና አፋር ክልሎች የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችና የኦፕቲካል ፋይበር የጥገና ሥራ ተጠናቀቀ፡፡
Next articleእውነት አሸባሪው ትህነግ ከግጭት መራቅ ይሆንለታል?