ከጅዳ እና አካባቢ ባሉ እስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገር ቤት መመለስ ዛሬ ይጀመራል፡፡

123

መጋቢት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ከታቀደው 102 ሺህ ኢትዮጵያውያን መካከል ከ80 ሺህ የማያንሱ የሚገኙት በጅዳ አካባቢ በሚገኙ እስር ቤቶች እና የማቆያ ማዕከላት ነው።
ዛሬ በሚደረጉ አራት በረራዎች ከጅዳ 1 ሺህ 438 በሳዑዲ አረቢያ በእስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ዜጎች ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከትላንት በስቲያ በጀመረው በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ሥራ በአንድ ቀን ከሪያድ 936 ኢትዮጵያዊን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል፡፡ ዛሬ ማለዳም 393 ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የብሔራዊ ምክክሩ አሳታፊነት የሚሳካው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቀናነትና በባለቤትነት ሂደቱን መደገፍ ሲችል ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
Next articleበአማራና አፋር ክልሎች የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችና የኦፕቲካል ፋይበር የጥገና ሥራ ተጠናቀቀ፡፡