
ባሕር ዳር: መጋቢት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በመላው ዓለም 1443ኛው ሂጅራ ታላቁ የረመዳን ወር ከቀናት በኋላ ይጀመራል፡፡ የእስልምና ሃይማኖት ከተገነባባቸው አምስት መሰረቶች አንዱ የረመዳን ወር ፆም ነው፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ ይኽንን የፆም ወር ከምግብ እና ከመጠጥ እንዲሁም ካላስፈላጊ ተግባሮች በመራቅ በፆም፣ በስግደት እና በጸሎት ያሳልፈዋል፡፡
1443ኛው ሂጅራ የረመዳን ወር ፆምን አስመልክቶ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸህ ሰዒድ ሙሃመድ ዑመር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው በቁርአናዊ ሕግ መነሻነት የረመዳን ወርን በተለየ መልኩ የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት፣ በማብላት፣ በማጠጣት እና በመደገፍ እናሳልፈዋለን ነው ያሉት፡፡ “ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ፆም ጋሻ ነው፤ አንዱ ፆመኛ በሆነ ጊዜ መጥፎ ቃል አይናገር ሌላ ሰው ሊሰድበው ወይም ሊገድለው ቢመጣ እንኳን እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል” ማለት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
“ረመዳን ቁርአን የወረደበት እና የጀነት በሮች የተከፈቱበት ነውና ወሩን በእስላማዊ ዱዓ እና በመረዳዳት ማሳለፍ ይገባል” ብለዋል፡፡
በረመዳን ወቅት እንቅስቃሴዎቻችን እስላማዊ ሥርዓት የተሞላባቸው እና ፆማችን በአሏህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን መትጋት እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ወቅት በሀገራችን በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ ችግር እንደተዳረጉም ጠቅሰዋል፡፡ ምዕመኑ በረመዳን ወቅት እስላማዊ አስተምህሮው በሚያዝዘው መሰረት ድጋፉን አጠናክሮ በመቀጠል ለወገን ደራሽ፣ ለአሏህም ታዛዥ መኾኑን ሊያረጋግጥ ይገባል ብለዋል፡፡ ሸህ ሰዒድ በረመዳን ፆም መግቢያ ላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ እየተመለሱ መሆኑን አውስተው ተመላሾች በሀገራቸው ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው ከጎናቸው መቆም እንደሚገባም ጠይቀዋል፡፡
በሌላ በኩል የሀገራችንን ሉዓላዊነት የሚዳፈሩ እና ሰላማችንን የሚያናጉ ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ሕጎችን በማዘጋጀት ሀገራዊ ቀውስ እንዲፈጠር የሚሠሩ የውጭ ኀይሎች መኖራቸውን ፕሬዚዳንቱ አንስተዋል፤ የሀገራችን የውስጥ ችግር የሚፈታው በውስጥ አንድነታችን እንጂ በውጭ ጣልቃ ገብነት አይደለም ሲሉም ገልጸዋል፡፡ መላው ሕዝብ ይህንን ድርጊት በማውገዝ በጋራ መቆም እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/