
መጋቢት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ ኮንግረንስ የሚቀነቀንላቸው ኤች.አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ሕጎችን ተፈጻሚነት እንዳይኖራቸው ለማስቆም በሀገር ውስጥና በውጪ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢፕድ እንደገለጹት፣ ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ይዘታቸው በሀገርም በሕዝብም ላይ ጫና የሚፈጥሩ ረቂቆች ናቸው። በመኾኑም የረቂቅ ሕጎችን ተፈጻሚነት እንዳይኖራቸው ለማድረግ በሳንፍራንሲስኮ፣ በዋሽንግተንና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ የሚገባ ነው።
ረቂቅ ሕጎቹ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ የኾነ ሁለገብ ጫና የሚፈጥሩ በመኾናቸው እነዚህ ጫናዎች ሕዝብንም ሀገርንም ይጎዳሉ ብለዋል አምባሳደሩ።
መንግሥት በተለያዩ ተቋማቱ ከሚሠራው ዲፕሎማሲያዊ ሥራ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንደ ሀገር ይህ ማዕቀብ ከተጣለ የሚያደርሰውን ችግር በመረዳት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ ነው፤ ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው ተግባር ነው።
ከዚህ በፊት በተካሄዱ እንቅስቃሴዎች ከሀገር ውጭ በተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፎችና የፊርማ ማሰባሰብ ሥራዎች እየተካሄዱ ነው። የተለያዩ የሴኔት አባላትን በማግኘትም እነሱ ላይ ተፅዕኖ የማሳረፍ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል አምባሳደር ዲና።
ረቂቆቹን የሚያንቀሳቅሱ ሰዎች ማንቀሳቀሱን እንደቀጠሉ ሰለኾነና በየደረጃው እስከመጨረሻው ይህንን ያስቀጥላሉ ተብሎ ስለሚታሰብ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ጥረት ይህ ረቂቅ አስፈላጊ አለመኾኑን ተረድተው እስኪተውት ድረስ ትግሉ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።
በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችሉ በቂ ምክንያቶች የሉም ያሉት አምባሳደሩ መንግሥት የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ መኾኑንም ተናግረዋል።
መንግሥት ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረግ በቂ ጥረት እያደረገ መኾኑንና በሀገር ደረጃ ሰላማዊ ምክክር ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ኮሚሽን በተመሠረተበት ኹኔታ ረቂቅ ሕጎችን በሰብዓዊ መብት ሕግ ጥሰት ሥም ለማፅደቅ መጣደፍ ተገቢ አለመኾኑን አመላክተዋል።
አምባሳደሩ እንዳሉት መንግሥት እያከናወናቸው ካሉ ተግባራት አኳያ የረቂቅ ሕጎቹ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል የሚኖረውንም ግንኙነት ይጎዳሉ። የኹለቱንም ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት የሚመጥንም አይደለም። በአጠቃላይ በሀገር ውስጥ የተጀመረውን የሰላም ጥረት የሚያደናቅፍ ነው ብለዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/