
መጋቢት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች ከነበርንበት አስከፊ ሁኔታ ወጥተን ለሀገራችን በመብቃታችን ተደስተናል ሲሉ ከስደት ተመላሽ ዜጎች ገለጹ፡፡
መንግሥት በእስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡
በሳዑዲ አረቢያ ከ750 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን እንደሚኖሩ የሚገመት ሲኾን፤ ከዚህም ውስጥ ከ450 ሺህ በላይ የሚኾኑት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ መኾኑ ይነገራል፡፡
በዚህም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በሳዑዲ አረቢያ ለእስር እንደተዳረጉ ይገለጻል፡፡
መንግሥት በእስር ቤት የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ የተለያዩ የዲፕሎማሲ ጥረቶችን ሲያከናውን ቆይቷል። ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለሱን ሥራ ዛሬ በይፋ ጀምሯል፡፡
ዛሬ ረፋዱ ላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት በሪያድ ከተማ ከሚገኙ ከእስር ቤቶች ወጥተው አዲስ አበባ የደረሱ ዜጎች የደስታ ስሜታቸውን በተለያየ መልኩ ገልጸዋል፤ የሀገራቸውን መሬት ሲስሙም ተስተውለዋል፡፡
ላለፉት ስድስት ወራት በእስር ቤት የቆየችው ሮዛ አሊ እና ከ10 ዓመታት በፊት ወደ ሳዑዲ አቅንታ ለእስር ተዳረጋ የቆየችው ሀገሬ አለባቸው ከበርካታ የችግር ጊዜያት በኋላ ወደ እናት ሀገራቸው በመመለሳቸው እጅግ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
መንግሥት ሌሎች በእስር ቤቱ የሚንገላቱ ወገኖችን በተቻለው አቅም እንዲመልሳቸውም ጥሪ አቅርበዋል።
በተመሳሳይ ፍሬ ሕይወት ዓለማየሁ እና ጌጤ አሰበም በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመሄዳቸው ለከፋ ስቃይ መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
“ሕገ-ወጥ ስደት በእኛ ይብቃ” ሲሉም ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን መልዕክት አስተላለፈዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ገንበቶ በበኩላቸው ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱ ዜጎችን ሁኔታ የማረጋገጥ ሥራ እየተከናወነ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ በዚሁ መሠረትም እናቶች፣ ሕጻናትና አረጋዊያንን በማስቀደም የመመለስ ሥራው መጀመሩን ተናግረዋል።
ስደተኞችን የመመለስ ሥራ ውስብሰብ ሂደት እንዳለው ጠቅሰዋል። በሳዑዲ አረቢያና በኢትዮጵያ መንግሥት መግባባት ተደርሶ በሳምንት 9 በረራዎችን በማድረግ ዜጎችን የመመለስ ሥራ መጀመሩን እንደገለጹ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/