
መጋቢት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁን የረመዳን ወር በተለያዩ ምክንያቶች በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን በመርዳት ማሳለፍ እንደሚገባ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ገለጹ።
ታላቁ የረመዳን ወር በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡
በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ በጉጉት በሚጠበቀው ረመዳን ቀኑን በጾም ማሳለፍ ምሽት ላይ ደግሞ ከቤተሰብና ከዘመድ ጋር ተሰብስቦ በአንድነት ማፍጠር የተለመደ ነው።
የእምነቱ ተከታዮች ወሩን በፍቅርና በፍስሃ ለመቀበል በየፊናቸው እምነቱ የሚያዘውን ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
የሃይማኖቱ ተከታዮች እንዳሉት፤ ታላቁ የረመዳን ወር ያለው ለሌለው በማካፈል አብሮነት የሚታይበት ጊዜ ነው፡፡
በመኾኑም በተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው የሚገኙ ወገኖችን ይበልጥ በማሰብና ያለንን በማካፈል ለማሳለፍ ተዘጋጅተናል ይላሉ፡፡
ሃጂ መንሱር ኢሳ እና አሊ መሐመድ፤ ረመዳን ኹሉም ልቡን በማጽዳት ከፈጣሪ ጋር የሚገናኝበት ወር በመኾኑ እርስ በርስ በመረዳዳትና አብሮነትን በማጠናከር ጾሙን ለማሳለፍ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
የረመዳን ወር በጎ ተግባር የሚከወንበት በመኾኑ ጾሙን አቅመ ደካማ ከኾኑ ወንድምና እህቶቻችን ጋር በአንድነት ለማሳለፍ መዘጋጀታቸውንም ነው የገለጹት፡፡
የሃይማኖቱ ተከታዮች ታላቁን የረመዳን ወር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በመንከባከብ ሊያሳልፍ እንደሚገባም ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በረመዳን ወር መልካም ነገር ማድረግና አዕምሮን ከመጥፎ ነገር ማጥራት የሚጠይቅ በመኾኑ ለሰላምና ለይቅርታ መዘጋጀት ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ አቶ ረዲ አሕመድ እና አልዬ ይመር ናቸው፡፡
ከዚህ አኳያ በኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግም ጠይቀዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/