በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኙ የመንግሥትና የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለአካባቢው ሕዝብ ተጠቃሚነት እንዲሠሩ ተጠየቀ።

138

ባሕር ዳር: መጋቢት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በዞኑ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የሚያንቀሳቅሱ በተለያዩ ጉዳዮች የሚሠሩ 20 መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንደሚገኙም ተጠቁሟል።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኙ የመንግሥትና የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች እየመከሩ ነው። ምክክሩ በዋናነት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ የተዘጋጀ ሲሆን በዞኑ የሚገኙ የመንግሥት ተቋማትና በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች እየሠሩ የሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ኀላፊዎች የውይይቱ ተሳታፊዎች ናቸው። የተሻሉ ተሞክሮዎችን በማስፋትና ትብብርን በማጠናከር የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ደግሞ የውይይቱ ዓላማ ነው።

በውይይቱም በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ችግሮች እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጽእኖ መኖር ድርጅቶች በገቡት ውል መሰረት ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ እንቅፋት ፈጥሮ መቆየቱ ተነስቷል። በተጨማሪም የተሻሉ ተሞክሮዎች ተከታትሎ ከማስፋትና ከመደጋገፍ አንጻር የሚታዩ ችግሮች እንዳሉና በቀጣይ መቀረፍ እንደሚገባ በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦች ናቸው።

በውይይቱ ንግግር ያደረጉት የማእከላዊ ጎንደር ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ እየሩስ መንግሥቱ በዞኑ የተለያዩ ቦታዎች በሚፈጠሩ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ችግሮች በርካታ ወገኖች ለተለያዩ ጉዳቶች እየተጋለጡ እንደሚገኙ አስታውቀው የማኅበረሰቡን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማፋጠን መንግሥት እየሠራ ካለው ተግባር በተጨማሪ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድርሻም ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል። በዞኑ የሚገኙ የመንግሥትና የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከመቸውም ጊዜ በተለየ ለአካባቢው ሕዝብ ተጠቃሚነት መሥራት እንዳለባቸው ጠይቀዋል።

በዞኑ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ያላቸው 20 ድርጅቶች 44 ፕሮጀክቶች ይገኛሉ። ድርጅቶቹ ከመንግሥት ጋር በመፈራረም በጤና፣ በሰላምና ደኅንነት፣ በትምህርት፣ በግብርና፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ ሴቶችና ህጻናት፣ አካል ጉዳተኞችና መሰል የልማት ተግባራት እየሠሩ የሚገኙ ናቸው።

ፕሮጀክቶቹ ከአምስት ወር እስከ 5 ዓመት የቆይታ ጊዜ ያላቸው ሰሆን ከ4 ሚሊዮን 331 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እያደረጉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

ዘጋቢ:- ሀይሉ ማሞ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleለአማራ እና ለአፋር ክልሎች ገቢዎች ቢሮ ከ17 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ እና የዓይነት ድጋፍ ተደረገ።
Next article“ታላቁን የረመዳን ወር በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን በመርዳት ማሳለፍ ይገባል” የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች