
መጋቢት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የገቢዎች ሚኒስቴር በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የአፋር እና የአማራ ክልል የገቢዎች ቢሮ ድጋፍ የሚውል የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በዚህም መሠረት ለአማራ ክልል የገቢዎች ቢሮ በገንዘብ 10 ሚሊየን ብር እና ግምታዊ ዋጋቸው 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁስ እንዲሁም ለአፋር ክልል የገቢዎች ቢሮ ደግሞ የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ እና ግምታዊ ዋጋቸው ከ515 ሺህ በላይ የሚያወጡ የተለየዩ የቢሮ ቁሳቁስ በድምሩ የ15 ሚሊየን ብር እና ከ2 የጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የዓይነት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው ድጋፉን ሲያስረክቡ እንደገለፁት ሚኒስቴሩ ከዚህ በፊትም ለኹለቱም ክልሎች የተለየዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል። አሁን የተደረገው ድጋፍ ለየት የሚያደርገው በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው የገቢ ተቋማትን በማጠናከር ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ ለመሰብሰብ እንዲያስችላቸው ታሳቢ ያደረገ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ ድጋፉ የገቢ ተቋማቱ በሙሉ አቅማቸው ገቢ መሰብሰብ እስኪችሉ ድረስ ቀጣይነት እንደሚኖረው አረጋግጠዋል፡፡
የተደረገው ድጋፍ ጉዳት ለደረሰባቸው በየክልሎቹ በሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች ሥር ለሚገኙ የገቢ ተቋማት በፍጥነት እንዲደርስ እና ወደሥራ እንዲገባ ማሳሰባቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃኀላፊ ዶክተር ጸጋ ጥበቡ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው የገቢ ተቋሙም በሙሉ አቅሙ ገቢ መሰብሰብ እንዲችል ድጋፉ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡ ድጋፉም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የአፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሐመድ ሐሰን ድጋፉ ለቀጣይ ሥራ አጋዥ መኾኑን ገልጸው ድጋፉ ጉዳት ለደረሰባቸው የገቢ ተቋማት በፍትሐዊነት ጥቅም ላይ እንደሚውል አረጋግጠዋል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/