የፌደሬሽን ምክር ቤት የክልሎችን በጀት ተመጣጣኝ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።

143

አዲስ አበባ: መጋቢት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በፌደሬሽን ምክር ቤት የበይነ መንግሥታት ፊስካል ወይም የወጭ እና ገቢ ግንኙነት የሚመራበትን አሠራር መፍጠር እና ቀጣይ አቅጣጫ በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

ባለፉት 30 ዓመታት የክልሎች የወጭና ገቢ ግንኙነቶች ምን ይመስላሉ በሚለው ጉዳይ እና በቀጣይ አቅጣጫዎችም ላይ ውይይት እየተደረገም ነው።

የበጀት አለመመጣጠንን ለመቅረፍ የሚያግዘዉ ይህ ግንኙነት የክልሎችን የአቅም ውስንነት በመመልከት ወጭ እና ገቢን ተመጣጣኝ ለማድረግ የሚያስችል መኾኑም ተጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት ተገቢዉን በጀት አላገኘሁም የሚሉ ተገቢ ቅሬታዎች እየተነሱ በመኾናቸው አሠራሮቻችን መፈተሽ እና ማረጋገጥ በማስፈለጉ በጉዳዩ ላይ ረቂቅ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት የምክር ቤቱ አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናግረዋል።

በቀጣይም ውይይት ከተደረገበት በኋላ በፌደሬሽን ምክር ቤት እንዲጸድቅ እንደሚቀርብ ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ኤልሳ ጉዑሽ-ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleንጋት ኮርፖሬት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት አልሚ ምግብ እና የስንዴ ዱቄት ድጋፍ አደረገ።
Next article“ሕገ ወጥ ንግድን መከላከል የሚቻለው የንግድ ሥርዓቱ ሲዘምን ብቻ ነው” የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር