
ሰቆጣ: መጋቢት 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የዘላቂ በጎ አድራጎት ድርጅት የቀድሞው ጥረት ኮርፖሬት የአኹኑ ንጋት ኮርፖሬት፥ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ከ1 ሺህ በላይ ኩንታል አልሚ ምግብ እና የስንዴ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል።
የኮርፖሬቱ ኦፕሬሽን አስተባባሪ ሀብታሙ መንግሥቱ እንዳሉት ኮርፖሬቱ ከዚህ በፊት ለሕግ ማስከበር ሥራ እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ214 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።
በንጋት ኮርፖሬት ሥር የሚገኙ እህት ኩባንያዎች ኀላፊዎች የተፈናቀሉ ወገኖች ያሉበትን ደረጃ በአካል በመገኘት ተመልክተዋል። እናቶች፣ ሕጻናት እና አረጋውያን ችግር ውስጥ መኾናቸውን መመልከት መቻላቸውን ነግረውናል።
በስደተኞች መጠለያ ጣብያ የንጽሕና፣ የማብሰያ እና ሌሎች ችግሮችን መመልከታቸውን የገለጹት የሥራ ኀላፊዎቹ ይህም በቀጣይ ተከታታይ ድጋፍ ለማድረግ እንዳነሳሳቸው ነው የገለጹልን።
የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አሥተዳዳሪና የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ሹመት ጥላሁን ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መኾኑን ገልጸዋል። ከችግሩ ስፋት አኳያ ግን አኹንም በቂ አለመኾኑን ገልጸዋል።
ተፈናቃዮችን ለማገዝ ኹሉን አቀፍ ድጋፍ አስፈላጊ ቢኾንም አልሚ ምግቦች እና የመጠለያ ድንኳን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እንደኾኑ ነው የጠቀሱት።
ካለው የተፈናቃይ ቁጥር 400 ድንኳን እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ሹመት አኹን ያለው የመጠለያ ድንኳን ከ20 የማይበልጥ መኾኑ ችግሩን ውስብስብ አድርጎታል።
በመኾኑም ድርጅቶች ይህንን ተገንዝበው ለእናቶች እና ሕጻናት አልሚ ምግቦች እና የመጠለያ ድንኳኖች ቅድሚያ ሰጥተው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/