
ደብረታቦር: መጋቢት 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 188/2011 የተቋቋመው የአማራ ክልል ግብርናና አግሮ ፕሮሰሲንግ ምርቶች ገበያ መዳረሻ ድርጅት አምራችና የምርት አቀናባሪዎችን ከሸማቹ ጋር በቀጥታ ማገናኘት፣ የግብይት ትስስር በመፍጠር የተረጋጋ የገበያ ሥርዓት መፍጠርና ለንግድና ግብይት ተዋናዮች የገበያ ክህሎት ማሳደግ ተጠቃሽ ዓላማዎቹ ናቸው፡፡
የአማራ ክልል ግብርናና አግሮ ፕሮሰሲንግ ምርቶች ገበያ መዳረሻ ድርጅት በዓላማዎቹና ተግባራቶቹ ላይ ከአጋር አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡
በግብርና ምርቶችና ገበያ ላይ ለተሳታፊዎች የሀገር ውስጥና የውጪ የገበያ ትስስር በማመቻቸት ገበያ ማረጋጋት፣ የውጭ ምንዛሬን ማሳደግና ሕዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ ከተልዕኮዎቹ የተሰጠው ድርጅቱ የአስመጪና ላኪዎች፣ የማኅበራትና የንግድ ድርጅቶችን ተባብሮ መሥራት በእጅጉ ይፈልጋል፡፡
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተዋቸው ወርቁ ከማኅበራትና ንግድ ቢሮ ጋር በመቀናጀት አቅራቢና ሸማችን የማገናኘት ሥራ እንደሚያከናውኑ ገልጸዋል፡፡
ከገንዘብ ተቋማት ብድርና የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን ማመቻቸት እንጠብቃለንም ብለዋል።
ድርጅቱን የማስተዋወቅ ሥራ እያከናወኑ እንደሚገኙም ጠቅሰዋል።
በውይይቱ የተሳተፉት የአማራ ክልል ሕብረት ሥራ ማኅበራት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የዝና ደስታ በሰጡት አስተያየት ድርጅቱ የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አኳያ በትብብር እንሠራለን ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ንግድ ቢሮ ኀላፊና የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ ድርጅቱ አሁን ላይ ያለውን የኑሮ ውድነትና የገበያ ችግር ለመፍታት መሥራት እንዳለበት ገልጸዋል።
ድርጅቱ የገበያ ክፍተትን ስለሚሞላና ስለሚያረጋጋ መንግሥትን ጨምሮ አጋር አካላት ዓላማውን በመገንዘብ ሊተባበሩትና ሊደግፉት እንደሚገባ አቶ ቀለመወርቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ:- ዋሴ ባየ -ከደብረታቦር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/