በሕዝብ ይሁንታ ያላገኙ ሕጎች መሻሻል እና ሁሉን አቃፊ የኾኑ ሕጎች ተግባራዊ መኾን እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

139

ባሕር ዳር: 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በፍትሕ ሚኒስቴር እና በክልል ፍትሕ ቢሮዎች መካከል የሕግና ፍትሕ ማሻሻያ የልምድ ልውውጥ መድረክ በባሕር ዳር ሲካሄድ እንደተገለጸው የልምድ ልውውጡ በፌዴራል ደረጃ ሲሠራ የነበረውን የሕግና የፍትሕ ማሻሻያ ሥራ ክልሎች ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ተግባራዊ ማድረግ እንዲችሉ ያስችላል።
በምክክሩ ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ፍትሕ ቢሮ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ዳይሬክተር ፌይሰል አዬ ከልምድ ልውውጡ ሕጎች ሲሻሻሉ ወይም ሲለወጡ ክልሎች ከፌዴራሉ መንግሥት ጋር ወጥ የኾነ አሠራር እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል ብለዋል። ከልምድ ልውውጡ ያገኙትን ሀሳብ በመቀመር የክልላቸውን ሕጎች እንደሚፈትሹም ጠቁመዋል።
በአማራ ክልል ምክር ቤት በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማእረግ የአፈ ጉባዔ የሕግ ጉዳዮች ዋና አማካሪ አለለኝ የኋላ ሁሉም ክልሎች ሕገ መንግሥታቸውን በማሻሻል የዜጎች መፈናቀልና መገደልን በማስቀረት እኩልነትን መፍጠር ይኖርባቸዋል ብለዋል። “ክልሎች ኹሉን አቃፊ ከኾነው የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገመንግሥት መማር አለባቸው” ብለዋል።
የወጡ ሕጎችም በአግባቡ ሥራ ላይ መዋል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ኅብረተሰቡም ኾነ ሕግን የሚያወጣው የመንግሥት አካል ሕግን ማክበር አለባቸው ነው ያሉት። ሕግን ማሻሻል ብቻ ሳይኾን የተሻሻሉ ሕጎችን በሥራ ላይ የሚያውሉት ተቋማት መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።
የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዓለምአንተ አግደው እንዳሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢፌዴሪ መንግሥት ቀልጣፋ ውጤታማና ተደራሽ የፍትሕ አገልግሎት ለመስጠት ዘርፈ ብዙ የሕግና የፍትሕ ማሻሻያ ሲያከናውን ቆይቷል።
የፍትሕ ተቋማት ግንባታና ማሻሻያ ሥራዎች መከናወናቸው፣ የፍትሕ ተቋማት ሙያዊ ነፃነታቸውን ጠብቀው እንዲሠሩ ለማስቻል አበረታች ጅምሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል። ክልሎች የተሻሻለውን የፍትሕ አሠራር ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። ሚኒስትር ዴኤታው የልምድ ልውውጡ በሀገርአቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ የሕግ አፈጻጸም እንዲኖር ያስችላል ነው ያሉት።
በልምድ ልውውጡ ከፌዴራል፣ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አሥተዳደሮች የተውጣጡ የፍትሕ የሥራ ኀላፊዎች፣ ባለሙያዎችና የፍትሕ ተጠሪ ተቋማት ተገኝተዋል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትሕና ዴሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እጸገነት መንግሥቱ “በፌዴራል ተቋማት መካከል፣ በፌዴራል፣ በክልል ቢሮዎችና በባለድርሻ አካላት ጠንካራ ቅንጅታዊ አሠራር እንዲፈጠር በማድረግ ጠንካራ የተቋማትና ሀገረ መንግሥት ግንባታ አውን እንዲኾን በቋሚ ኮሚቴው በኩል የሚደረገው የክትትልና የቁጥጥር ሥራ ጠንክረን እንሠራለን” ብለዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበአሜሪካ ከሚገኙ የኮሚዩኒቲ አደረጃጀት ኃላፊዎች፣ የታስክ ፎርስና ከሲቪክ ማኅበራት አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ
Next articleዜና መጽሔት ባሕር ዳር: መጋቢት 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ)