በአሜሪካ ከሚገኙ የኮሚዩኒቲ አደረጃጀት ኃላፊዎች፣ የታስክ ፎርስና ከሲቪክ ማኅበራት አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ

178

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋና በመንግሥታቱ ድርጅት የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በመላው አሜሪካ ከሚገኙ የኮሚዩኒቲ አደረጃጀት ኃላፊዎች፣ የታስክ ፎርስ፣ የሲቪክ ማኅበራት አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ጋር በበይነ መረብ ውይይት ተደርጓል።
አምባሳደር ፍጹም ባስተላለፉት መልዕክት በአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት HR.6600 እና S.3199 በሚል በኢትዮጵያ ላይ ለማሳለፍ የቀረቡ ረቂቅ ህጎች የአገርን ሉዓላዊነት የሚጋፉ፣ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በእጅጉ የሚያሻክርና ዳያስፖራውንም ከአገሩ ጋር ያለውን ትስስር የሚበጣጥስ አደገኛ እርምጃ ነው ብለዋል።
እንደዚህ አይነት ወገንተኝነት የሚታይባቸው ሕጎች ወደነበረበት ጠንካራ መስተጋብር እየተሸጋገረ ያለውን የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ወዳጅነት በእጅጉ እንደሚጎዳው ገልጸዋል።
መንግሥት በማንም ግፊት ሳይሆን ለአገር አንድነትና ሰላም ሲል በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ ባለበት ወቅት የእጅአዙር ጫና ለማድረግ መሰል አካሄዶችን ይዞ መምጣት ገንቢ አለመሆኑን ገለጸው ይህም ፈጽሞ ተቀባይነት እንደሌለው ነው ያስረዱት።

በመላው አሜሪካ የሚገኘው ዳያስፖራ እያደረገ የቆየውን ታሪክ የማይዘነጋው የአገር ዘብነት፤ እነዚህ ቢሎች እንዳይጸድቁ በማድረግ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።
በእለቱ መልዕክት ያስተላለፉት በመንግሥታቱ ድርጅት የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ እንዳሉት ዳያስፖራው በሀገር ላይ የሚሰነዘር የውጭም ሆነ የውስጥ ጫና በአንድነት ቆሞ እንዲመክት ጠይቀዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሀገር እንደማይኮረፍ፤ ከመንግሥት እርምጃዎች ጋር በተገናኘ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች በአገር ቀጣይነት ላይ የተደቀኑትን ረቂቅ ህጎች እንዳይጸድቁ ከመታገል አንደማያቆማቸው ገልጸዋል።
በተለይም በየአካባቢያቸው የሚገኙ ተመራጮችን በስልክና በኢሜል፣ ፔቲሽን በመፈረም እንዲሁም በአካል በማግኘት ትክክለኛ መረጃ እንዲኖራቸው በማድረግ ለመጽደቅ በሂደት ላይ የሚገኙት ረቂቆች እንዲመክኑ የጀመሩት ሥራ እንደሚያጠናክሩ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።
Next articleበሕዝብ ይሁንታ ያላገኙ ሕጎች መሻሻል እና ሁሉን አቃፊ የኾኑ ሕጎች ተግባራዊ መኾን እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡