ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።

130

ባሕር ዳር: 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጂቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።
የጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።
ፕሬዚዳንቱ ዛሬ የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝተዋል።
ከጉብኝቱ በኋላ የሁለቱ ሀገሮች መሪዎች በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም እንደገለጹት፤ መሪዎቹ በዋናነት ኢትዮጵያና ጂቡቲ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ፣ ሰላምና ደኅንነት እንዲሁም በሌሎች በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም ቀጣናዊ ትስስር ስለሚጠናከርበት ሁኔታም መምከራቸውን ገልጸዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የዘንድሮ የዒድ በዓል ኢትዮጵያ ለእስልምና ሃይማኖት ባለውለታ መኾኗን በሚያሳይ መልኩ ይከበራል” ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ
Next articleበአሜሪካ ከሚገኙ የኮሚዩኒቲ አደረጃጀት ኃላፊዎች፣ የታስክ ፎርስና ከሲቪክ ማኅበራት አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ