በጦርነቱ ተፈናቅለው ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመርዳት የቆየ የእርስ በርስ የመደጋገፍ ባሕልን ማጠናከር እንደሚገባ የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ።

122

ሰቆጣ: መጋቢት 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የከፋ ችግር ላይ ለወደቁ ሴቶች እና ሕጻናት 3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት እና ለ300 እናቶች ደግሞ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
በክልሉ መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶችእስካሁን 200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ቢያደርጉም ድርጅቶቹ የወሰዱት ስምምነት ከተከሰተው ችግር ስፋት ጋር የሚጣጣም ባለመኾኑ ችግሩን መፍታት አለመቻሉን የቢሮው ምክትል ኀላፊ ዝና ጌታቸውገልጸዋል።
መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች፣ የፌዴራል እና የክልል ተቋማት እና ባለሀብቶች አኹንም ድጋፋቸዉን አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ኀላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል። ማኅበረሰቡም የቆየ የእርስ በርስ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት ባሕሉን ማጠናከር እንደሚገባ ጠይቀዋል።
የክልሉ ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከመጠለያ ጣብያ ውጭ የሚገኙ ሕጻናት እና እናቶች ጭምር የችግሩ ሰለባ መኾናቸውን ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ማቅረቡን ወይዘሮ ዝና ገልጸዋል።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደርን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ድጋፍ ቢያደርግም ከችግሩ ስፋት ጋር ተመጣጣኝ አለመኾኑን ነው የገለጹት።
በቀጣይ የችግሩን ጥልቀት ተመልክቶ ሕጻናትን እና እናቶችን ሊታደግ እንደሚገባ ኀላፊዋ ጠይቀዋል።
በክልሉ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት “የዕለት ምግብ ያስፈልጋቸዋል” ተብለው ከተለዩት ዜጎች ውስጥ
➸ 50 በመቶ ሴቶች ናቸው
➸ 400 ሺህ የሚኾኑት ደግሞ ሕጻናት መኾናቸውን
ከአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ካባ ሲሳይ ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ድጋፍ ቢደረግም ከተፈናቃዩ ቁጥር እና ከችግሩ አሳሳቢነት አኳያ በቂ አለመኾኑን ገልጸዋል።
ሴቶች እና ሕጻናት ላይ ትኩረት አድርገው የሚሠሩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማት አኹንም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
➸ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በሚገኙ ሦስት መጠለያ ጣብያዎች ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ የተፈናቃዩ ቁጥር ከ65 ሺህ 700 በላይ ደርሷል። ከዚህ ውስጥ:-
➸18 ሺህ የሚያጠቡ ናቸው
➸ከ1 ሺህ 100 በላይ አረጋውያን ሲኾኑ
➸ 590 የሚኾኑት ደግሞ አካል ጉዳተኞች መኾናቸውን ከብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ የተገኘ መረጃ ይጠቁማል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበኩር ጋዜጣ መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ዕትም
Next article“የዘንድሮ የዒድ በዓል ኢትዮጵያ ለእስልምና ሃይማኖት ባለውለታ መኾኗን በሚያሳይ መልኩ ይከበራል” ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ