በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማት መልሶ በማቋቋም ስልጠና ለማስጀመር እየተሰራ ነው።

174

ባሕረ ዳር: መጋቢት 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ እና በአፋር ክልል በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማት መልሶ በማቋቋምና ተቋማቱን በማስተሳሰር በአጭር ጊዜ ውስጥ ስልጠና ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አሰታወቀ።

ተቋማት በሚኖራቸው የሰልጣኞች ቅበላ አዲሱን የሙያ ደረጃ መሰረት እንደሚያደርጉም ተገልጸዋል።

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከክልሎች ና ከከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ አመራሮች ጋር በዘርፉ ቁልፍ ተልዕኮዎች፣ የሪፎርም ተግባራትና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በምክክር መድረኩ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት፣ የዘርፉ ፖሊሲና ስትራቴጂ ማሻሻያ ሀሳቦች፣ ተቋማትን በተልዕኮና ትኩረት መስክ ማደራጀት፣ በጦርነት ምክንያት በዘርፉ የደረሰ ጉዳትን የተመለከተ ጥናት እንዲሁም የ2014 የመቁረጫ ነጥብና በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማት መልሶ ለማደረጃት በተከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በከር ሻሌ (ዶ.ር) በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፤ በዚህ ዓመት ተቋማት በሚኖራቸው የሰልጣኞች ቅበላ አዲሱን የሙያ ደረጃ መሰረት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

ሰልጣኞች ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተግባቦት፣ የሥራ ፈጠራና ሰልጣኞች የአገር ፍቅር እንዲኖራቸው ያለሙ የትምህርት ዓይነቶች ይሰጣሉ።

ተቋማት በየደረጃው የየአካባቢውቸውን ፀጋና የሥራ ገበያ ፍላጎት መሰረት አድርገው ቅበላቸውን ሊያከናውኑ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በአማራ እና በአፋር ክልል በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማት መልሶ ለማቋቋም እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ እና ተቋማቱን በማስተሳሰር በአጭር ጊዜ ውስጥ ስልጠና ለማስጀመር እየተሰራ ነው ተብሏል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleʺ በሚያልፈው ዓለም የማያልፈውን አድርግ”
Next articleበኩር ጋዜጣ መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ዕትም