
ባሕር ዳር: መጋቢት 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተቋሙ በበለፀጉ ሶፍትዌሮች አጠቃቀም ዙሪያ ሲሰለጥኑ የቆዩና ከሁሉም ክልሎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች የውኃ ሴክተር ተቋማት የተውጣጡ 120 ባለሙያዎችን ዛሬ አስመርቋል።
የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምሳደር አስፋው ዲንጋሞ በዚሁ እንደገለፁት፤ የበለፀጉት ሶፍትዌሮች በሀገሪቱ የውኃ ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ የሚስተዋሉ የዲዛይን ጥራት ችግርና የጊዜ መጓተትን ለማስቀረት አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።
በተለይም የመጠጥ ውኃ ፕሮጄክቶች ተደጋጋሚ የዲዛይን ማሻሻያ፣ የጥራት ጉድለትና በተያዘላቸው ጊዜ ባለመጠናቀቅ መንግሥትን ለተጨማሪ ወጪ እየዳረጉና የመልካም አስተዳደር ችግር መንስኤ መሆናቸውን አንስተዋል።
የዘርፉን ችግር ለመፍታት ጥራት ያለው ዲዛይን በውስጥ ባለሙያዎች እንዲዘጋጅና ተደጋጋሚ የዲዛይን ማሻሻያ እንዳይኖር የሚያስችል ስርዓት የሚዘረጉበት ሶፍትዌር መገንባቱን ነው ያወሱት።
የሕዝቡን የመጠጥ ውኃ ፍላጎት ለማሟላትና በዘርፉ የሚነሱ ጥያቄዎችን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና ሶፍትዌሮችን በመጠቀም በተቀመጠላቸው ጊዜ ለመመለስ ጭምር የሚረዳ መሆኑን አመልክተዋል።
“የፕሮጀክቶችን የኮንትራት አስተዳደር ከማዘመን ባለፈ ስራውን ሊመራ የሚችል የሰው ኀይል አቅም ለመገንባት ግብ አስቀምጠን እየሠራን ነው” ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው።
በሚኒስቴሩ የስልጠና አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ሉሌ በበኩላቸው እየተሠሩ ያሉ የውኃ ፕሮጀክቶች ላይ የሚታየውን የዲዛይንና የግንባታ ጥራት ችግር ለመፍታት የሚያስችሉና ወቅቱን ያገናዘቡ ሶፍትዌሮች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሶፍትዌሮቹ የሥራ ተቋራጮችን ለመቆጣጠር ጭምር የሚረዱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
የግንባታ ውል ስምምነቶችን ጥራትና የአቅርቦት፣ የግዥ ሂደትና የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራትንም በበቂ እውቀት ላይ ተመስርቶ ለመከታተል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ላይ ሙያተኞቹ ተገቢውን ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/