ዘምዘም ባንክ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለወደሙ የደሴ ከተማ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አደረገ፡፡

267

ደሴ: መጋቢት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዘምዘም ባንክ ከወለድ ነጻ ቅርንጫፉን በደሴ ከተማ በከፈተበት ወቅት በደሴ ከተማ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ የሚውል 150 ሽህ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ደሴ ከተማ ለረጅም ዓመታት የንግድ ሥርዓት ሲከናወንባት የኖረች ከተማ እንደመኾኗ ዘመናዊ የፋይናንስ ተቋማት እንደሚያስፈልጓት ተገልጿል፡፡ ከወለድ ነጻ የሆነ ባንክን እውን ለማድረግ ረጅም ጊዜ ፈጅቷል ያሉት የዘምዘም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ከድር በደዊ ዘምዘም ባንክ ይህንን ጥያቄ የመለሰ ባንክ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

ባንኩ የንዋይ ግልጋሎት ከመስጠት ባለፈ ማኅበራዊ አገልግሎትም መስጠት ስላለበት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ የሚውል ገንዘብ ለከተማ አሥተዳደሩ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ባንኩ በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ለማገልገል ይሠራል ነው ያሉት፡፡

የደሴ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ፍቅር አበበ በከተማዋ ያሉ ትምህርት ቤቶች በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በመዘረፋቸውና በመውደማቸው የመማር ማስተማር ሥራውን አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል፡፡ በተለይም ቤተሙከራዎችን በቀላሉ ወደ አገልግሎት መመለስ እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡ ዘምዘም ባንክ ላደረገው ድጋፍም አመስግነዋል፡፡

ባንኩ በፋይናንስ ሴክተሩ ተወዳዳሪ ኾኖ እንዲዘልቅ ከተማ አሥተዳደሩ የሚጠበቅበትን እገዛ እንደሚያደርግ ነው የገለጹት፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀን አምባቸው-ከደሴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአሚኮ ለኅብረተሰብ ለውጥ እንዲተጋና በአርዓያነት የሚጠቀስ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖረው እንደሚሠራ የኮርፖሬሽኑ ቦርድ ሰብሳቢ ግርማ የሺጥላ ገለጹ፡፡
Next articleበውኃ ፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋሉ የዲዛይን ጥራት ችግርና የግንባታ ጊዜ መጓተት ለማስቀረት የሚያስችሉ ሶፍትዌሮችን ማበልፀጉን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።