
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አዲሱ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የቦርድ አመራር አባላት ኮርፖሬሽኑን ጎብኝተዋል፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ኾነው የተሾሙት አቶ ግርማ የሺጥላ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት “ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን” የሚለው የአሚኮን መሪ ሐሳብ ለማሳካት እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡ የቦርድ ሰብሳቢው እንዳሉት ቦርዱ ኮርፖሬሽኑ የጎደለውን ለመሙላት ጠንክሮ ይሠራል። ተቋሙን ወደፊት የሚያሻግር እቅድ ታቅዶ እንደሚሠራ የገለጹት የቦርድ ሰብሳቢው በተለይ የኮርፖሬሽኑን የሰው ኀይል የማጎልበት ተግባር እንደሚከናወን ተናግረዋል።
አቶ ግርማ እንዳሉት ለኅብረተሰብ ለውጥ የሚተጋ የሰው ኀይል ይገነባል። አሚኮ አርዓያ የኾነ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖረው ተግተው እንደሚሠሩም የቦርድ ሰብሳቢው ጠቁመዋል። የኮርፖሬሽኑ ነጻነት እንዲጠበቅ እንደሚሠሩም ነው ያብራሩት።
የቦርዱ አባላት በወርቃማ ቀለም የሚፃፍ ትርጉም ያለው ሥራ ለመሥራት ቁርጠኛ መኾናቸውን ገልጸዋል።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥዬ ኮርፖሬሽኑ በ27 ዓመታት ጉዞው ያለውን ተደራሽነት ለቦርዱ አባላት አብራርተዋል።
አሚኮ ከጊዜ ወደ ጊዜ አድማሱን እያሰፋ መኾኑንም አስረድተዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንዳሉት አሚኮ በውጪ ሀገራት የራሱ ዘጋቢዎች እንዲኖሩት እየሠራ ነው። ኮርፖሬሽኑ የበለጠ ተደራሽ፣ ጥራት ያለውና የተሻለ የሕዝብ አገልጋይ እንዲኾን ቦርዱ እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። አሚኮ በአዲስ አበባ የራሱ ሕንጻ እንዲኖረው ቦርዱ መሥራት እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/