“ኤችአር 6600 ረቂቅ ሕግ ኢትዮጵያውያንና ምሥራቅ አፍሪካውያንን ለመከፋፈልና ለማዳከም የተዘጋጀ ነው” ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ

357

መጋቢት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “ኤችአር 6600 ረቂቅ ሕግ ኢትዮጵያውያንና ምሥራቅ አፍሪካውያንን ለመከፋፈልና ለማዳከም የተዘጋጀ ነው”ስትል ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ገለጸች።

ዳያስፖራው ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል የተዘጋጀውን ሕግ በአንድነት በመቆም እንዲታገል ጥሪ አቅርባለች።

ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ‘ኤችአር 6600’ ረቂቅ ሕግ አስመልክቶ እንዳለችው ሕጉ ‘በኢትዮጵያ ሰላም፣መረጋጋትና ዴሞክራሲ አመጣለሁ” ቢልም በተቃራኒው ኢትዮጵያን የሚጎዳ መኾኑን ገልጻለች።

“ኤችአር 6600” ረቂቅ ሕግ ኢትዮጵያውያንና ምሥራቅ አፍሪካውያንን ለመከፋፈልና ለማዳከም የተዘጋጀ ነው ብላለች።

የሕጉ አርቃቂዎች “ስለ ኢትዮጵያውያን፣ኤርትራውያንና ምሥራቅ አፍሪካውያን ግድ አይሰጣቸውም፤ አሁንም በኢትዮጵያ ጦርነቱን የጀመረው አሸባሪው ሕወሓት መኾኑን ኹልጊዜ እንዳላየ እያለፉት ነው” ስትል ገልጻለች።

የአሸባሪው ሕወሓት እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ያለው ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ሥራ ይበልጥ አስቸጋሪ እንዳደረገው አመልክታለች።

የረቂቅ ሕጉ አርቃቂዎች የአሸባሪው ሕወሓት ደጋፊዎችና ቡድኑ የፈጸማቸውን ወንጀሎች መሸፈን የሚፈልጉ መኾናቸውንና ሕጉ የተጻፈውም የአሸባሪው ቡድን ደጋፊዎች ለተወሰኑ የኮንግረስ አባላት በከፈሉት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መኾኑን ተናግራለች።

“ኤችአር 6600” አሸባሪው ሕወሓት ላይ ምንም አይነት እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርግ አንቀጽ የለም ብላለች።

ረቂቅ ሕጉ በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ያሻሽለዋል የሚሉ አንዳንድ ወገኖች አሉ፤በተቃራኒው ሕጉ በኢትዮጵያ ያለውን ችግር የሚያባብስ እንደኾነ አመልክታለች።
በማዕቀብ ለውጥ እንደማይመጣና ችግር አባባሽ መኾኑን ከኢራቅ፣ሊቢያ፣አፍጋኒስታንና ሶሪያ የተሻለ የታሪክ ማሳያ ሊኖር እንደማይችል ገልጻለች።

ረቂቅ ሕጉ በአሜሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የማስቆም ዓላማ ያለው ነው ብላለች።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለመከፋፈል የተዘጋጀውን ኤች አር 6600 እንዳይጸድቅ ዳያስፖራው በአንድነት በመቆም እንቅስቃሴ ሊያደርግ እንደሚገባ መግለጿን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እውነት ያሸነፋል ኢትዮጵያም ሰላም የምትኾንበት ጊዜ ሩቅ እንደማይኾን ነው የገለጸችው፡፡

ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ከነገ በስቲያ ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎች በመቃወም በዋሺንግተን ዲሲ የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ ‘ካፒቶል ሂል’ ፊት ለፊት በሚካሄደው ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በመሳተፍ ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርባለች።

የ’ኤች አር 6600’ ረቂቅ ሕግን የሚቃወም ሰልፍ ትናንት በካሊፎርኒያ ግዛት ሳንፍራንሲስኮ ከተማ መካሄዱ የሚታወስ ነው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የጎንደር ሕዝብ ተራ የኾነ ፓለቲካ ውስጥ ገብቶ ከአማራነትና ከኢትዮጵያዊነቱ ማማ አይወርድም” የጎንደር የሰላም እና የዕድገት ማኅበር ጉባኤ ተሳታፊዎች
Next articleአሚኮ ለኅብረተሰብ ለውጥ እንዲተጋና በአርዓያነት የሚጠቀስ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖረው እንደሚሠራ የኮርፖሬሽኑ ቦርድ ሰብሳቢ ግርማ የሺጥላ ገለጹ፡፡