
ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ቀለመወርቅ ምሕረቴ የኑሮ ውድነቱን አስመልክቶ ከክልሉ ምክር ቤት አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አቶ ቀለመወርቅ እንዳሉት በክልሉ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች በዋጋ ጭማሬ ምክንያት ኑሮውን መሸከም አቅቷቸዋል፡፡ በባለፈው ዓመት ከዚህ ወቅት ጋር ሲነፃጸር የብርእ ሰብሎች 38 በመቶ፣ የአገዳ ሰብሎች 66 በመቶ እና የቅባት እህሎች 40 በመቶ የጨመሩ ሲኾን የኢንዱስትሪ ምርቶች ደግሞ ምግብ ነክ የኾኑት 44 በመቶ እና የግንባ እቃዎች 49 በመቶ መጨመራቸውን አስረድተዋል፡፡
በሀገር ደረጃ ካለው የዋጋ ግሽበት አንፃር ሲታይ የአማራ ክልል ከፍ የሚል መኾኑን አቶ ቀለመወርቅ በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል፡፡
ለዚህም በገበያ ውስጥ የምርት እጥረት መኖሩ እና አንዳንድ የንግድ ማኅበረሰብ ክፍሎች ምርትን መደበቃቸው እንደ ምክንያት የሚነሳ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ የዓለምአቀፍ ሁኔታም በዋጋ ጭማሬው ላይ የራሱን አሉታዊ ተፅእኖ መፍጠሩን ኀላፊው ገልጸዋል፡፡
የዋጋ ግሽበቱን ለመቀነስ ሁሉንም ተቋማት ያካተተ ሥራ እየተሠራ መሆኑን አቶ ቀለመወርቅ ተናግረዋል፡፡ የትርፍ ህዳግን ለመወሰን ሥልጣን የተሰጠው አካል ባለመኖሩ በነፃ ገበያ ምክንያት ያለአግባብ ዋጋ ይጨመራል ነው ያሉት፡፡
ገበያውን ለማረጋጋት የተዋቀረው ግብረ ኃይል ያለአግባብ ምርትን በሚደብቁ አካት ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም 1 ሺህ 895 ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን እና በ1 ሺህ 862 ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ደግሞ አሥተዳደራዊ እርምት መወሰዱን ነው ያስረዱት፡፡ በተወሰደው እርምጃም የተሻለ ውጤት መገኘቱን አቶ ቀለመወርቅ አስረድተዋል፡፡
መሰረታዊ ምርትን ለማግኘት የተሻለ ኮታ እንዲመደብ መደረጉንም አስገንዝበዋል፡፡ይኹን እንጂ የመጨረሻ መፍትሔ አለመኾኑን ነው የተናገሩት፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ለመሠረታዊና ለሸማች ማኅበራት የተዘዋዋሪ ብድር መሰራጨቱን ጠቁመዋል፡፡ የሰንበት ቀን ገበያ በሁሉም ዞኖች እንዲከፈት ተደርጓልም ነው ያሉት፡፡ አምራቾች በቀጥታ ለሸማቹ እንዲያደርሱም ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑን ኀላፊው ገልጸዋል፡፡
በወረራ ሥር የነበሩ 89 ሺህ 844 ነጋዴዎች የተለዩ ሲሆን ከጥር ጀምሮ የንግድ ፈቃዳቸውን ማደስ የሚችሉት በቅጣት ቢኾንም ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በመነጋገር እስከ ሰኔ 30 ድረስ ያለቅጣት የንግድ ፈቃዳቸውን እንዲያድሱ ሁኔታው የተመቻቸላቸው መኾኑን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በክልሉ መንግሥት ፈቃድ መሰረት እነዚህ ነጋዴዎች ከአገልግሎት ክፍያ ነፃ በኾነ መልኩ የንግድ ፈቃዳቸውን እንዲያድሱ መደረጉን ኀላፊው ጠቁመዋል፡፡ እስካሁን ድረስ 21 ሺህ 169 ነጋዴዎች የንግድ ፈቃዳቸውን ማደሳቸውንም አስረድተዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ብሪክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/