“ከዒድ እስከ ዒድ ወደ ሀገር ቤት” የተሰኘው ሀገራዊ ጥሪ ስኬታማ ለማድረግ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

116

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “ከዒድ እስከ ዒድ ወደ ሀገር ቤት” የተሰኘው ሀገራዊ ጥሪ መርኃግብር አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በመግለጫው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዳሉት በሀገራዊ ጥሪው በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በወሳኝ ወቅት ለሀገራቸው ያላቸውን ድጋፍ እና ፍቅር በተግባር ያሳዩበት እንደነበር አስታውሰዋል።
“ከዒድ እስከ ዒድ” በሚል ስያሜ የሚካሄደው ታላቁ የኢትዮጵያውያን ጉዞ ኢትዮጵያ በሃይማኖት፣ በታሪክና በባህል ያሏትን እሴቶች ለዓለም የምታሳይበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መርኃ ግብሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት በኀላፊነት እንዲሠሩም ጠይቀዋል።
መርኃ ግብሩ ከረመዳን ፆም ኢድ ኣልፈጥር ጀምሮ እስከ ዒድ አልድሃ (አረፋ) በዓል ድረስ ይቆያል፡፡ “ከዒድ እስከ ዒድ” ሀገራዊ ጥሪውን ስኬታማ ለማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲኹም የጎረቤት ሀገራት እና የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ዜጎች የዒድ በዓልን በኢትዮጵያ እንዲያከብሩ ይጋበዛሉ ተብሏል።
በቆይታቸዉ ዳያስፖራው በግጭትና ድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ በመገንባት እና በአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ተሳትፎ እንዲኖራቸው በማስቻል ለወገኖቻቸው ያላቸውን አለኝታነት እንደሚያጠናክሩም ተመላክቷል። በዚህ ሀገራዊ ጥሪ፥ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ከማጠናከር ባለፈ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎሚያሳዊና ፖለቲካዊ ግቦችን ለማስፈፀም ጥረት እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

በታላቁ ረመዳን ወር ገቢራዊ የሚደረገው “ከዒድ እስከ ዒድ ወደ ሀገር ቤት” የተሰኘው ሀገራዊ ጥሪ ስኬታማ ለማድረግ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
“ከዒድ እስከ ዒድ” ሀገራዊ ጥሪ የኮሚቴ ጣምራ ሊቀ መንበር ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ እንዳሉት፥ በዓሉ ኢትዮጵያ ያላትን የእስልምና ሃይማኖት ቱባ እሴቶች ለማስተዋወቅ እና በጎ ተፅዕኖን በወዳጅ ሀገራት ዘንድ ለመፍጠር ይቻል ዘንድ አበክሮ ይሠራል ብሏል።
መርኃ ግብሩን በበላይነት የሚያስፈፅሙት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራው ነባሩ ብሔራዊ ኮሚቴ ባለበት ቀጥሏል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ብርቱካን አያኖ፣ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ እና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ሥራውን በጥምረት ይመራሉ ተብሏል።
ዘጋቢ፡- ወርቃየሁ ቸኮል -ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ሕዝብ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ አመኔታ የሚያጣ ከሆነ ተሻጋሪ የኾነ ችግርን ሊያስከትል ይችላል” የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
Next articleከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው በመመለስ በዘላቂነት ለማቋቋም መንግሥት እንደሚሠራ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ።