“ሕዝብ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ አመኔታ የሚያጣ ከሆነ ተሻጋሪ የኾነ ችግርን ሊያስከትል ይችላል” የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

172

ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች በጦረነት ሥነልቦና ውስጥ ኾነው ፈተና መውሰዳቸው እንደጎዳቸው ቢሮው ገልጿል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ.ር) የ12ኛ ክፍል ፈተናን አስመልክቶ ከክልሉ ምክር ቤት አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ መምህራን፣ የትምህርት የሥራ ኀላፊዎች፣ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ አመኔታ የሚያጡ ከሆነ ተሻጋሪ የኾነ ችግርን ሊያስከትል ይችላል ብለዋል፡፡
ተማሪዎች ደክመው፤ ጥረው ባጠኑት ልክ በሚያገኙት ውጤት አመኔታ ሊያሳድሩ እንደሚገባም ነው ኀላፊው ያስረዱት፡፡
መምህራንም ባስተማሩት ልክ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡
የትምህርት የሥራ ኀላፊዎችም በአመራር ዘመናቸው የሠሩትን ውጤት ማየት ስለሚፈልጉ በሚመጣው ውጤት አመኔታን የማያሳድሩ ከሆነ እንደ ሀገር ችግር ሊያጋጥም ስለሚችል ችግሩ ሊፈታ ይገባል የሚል የክልሉ አቋም እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡
ሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ ውጤቶችን ተንትኖ የውሳኔ ሀሳብ ካቀረበ በኋላ ትምህርት ሚኒስቴር ውጤቶቹን ተንትኖ ፍትሐዊ የኾነ የመቁረጫ ነጥብ መወሰንና ግልጸኝነት የመፍጠር ኀላፊነት እንዳለበት አብራተዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር እየተፈጠረ ያለውን የእምነት ማጣት ጉዳይ ግልጽ አሠራር በመዘርጋት መተማመን መፍጠር እንዳለበት ክልሉ ያምናል ብለዋል፡፡
ዶክተር ማተብ ውጤቱ ከተገለጸ በኋላ ቢሯቸው ባደረገው ግምገማ የክልሉ ተማሪዎች ውጤት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልሉ ዝቅ ያለ መኾኑን ጠቁመዋል፡፡ ውጤቱ እንዲስተካከል ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባበት ወቅት እንዲራዘም እና ጉዳዩ እንዲጣራ ለትምህርት ሚኒስቴር በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረባቸውን ዶክተር ማተብ አስታውሰዋል፡፡
ሂደቱን የሚያጣራ ግብረ ኃይልም ወደ ሚኒስቴሩ መላካቸውን አስረድተዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የክልሉ ተማሪዎች በጦርነቱ በመጎዳታቸው እና ሳይዘጋጁ በመፈተናቸው በተለየ መንገድ ጎድቷቸዋል የሚል አቋም እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡ ችግሮቹን ለመፍታት በሰከነ መልኩ የተማሪዎቹንና የሕዝቡን መብት ለማስከበር መሥራት እንዳለበት ታምኖ እንቅስቃሴ እየተደረገ ስለመኾኑም ነው ያስገነዘቡት፡፡
ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የፌዴራል መንግሥት በጀት እንዲመድብ የምክር ቤት አባላት ጠየቁ።
Next article“ከዒድ እስከ ዒድ ወደ ሀገር ቤት” የተሰኘው ሀገራዊ ጥሪ ስኬታማ ለማድረግ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡