
ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው እንደቀጠለ ነው።
በጉባኤውም የፌዴራል መንግሥት
ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን በጀት እንዲመድብ የምክር ቤት አባላት ጥያቄ አንስተዋል።
የምክር ቤት አባላት ያነሷቸው ጥያቄዎችና ሐሳቦች
በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ከንጹሐን ለይቶ በመያዝ በኩል ክፍተት አለ። ወንጀለኛ ይያዙ፣ ነገር ግን አያያዙ ንጹሐንን እንዳይጨምር ጥንቃቄ መደረግ አለበት።
በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የፀጥታ ኃይሉን ስምሪት በማጠናከር ቀጣናውን ማስተካከል ይገባል። የሽብር ቡድኑ እንዳይነሳ አድርጎ ለመስበር ማኅበረሰቡን አስተባብሮና አሰልጥኖ መሥራት ይገባል።
ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ የፌዴራል መንግሥት በጀት የማይመድብለት ለምንድን ነው?
በክልሉ ያለው የፀጥታ ችግር በምን መንገድ ነው የሚስተካከለው፤ ለማስተካከል ለምን አይሠራም፣ የክልሉ መንግሥት አቋሙና አቅጣጫው ምንድን ነው?
በክልሉ ያልተለቀቁ አካባቢዎች አሉ፤ ንጹሐን ችግር ውስጥ ናቸው፣ በቂ ምግብ እየቀረበላቸው አይደለም። አካባቢው ነፃ ካልወጣ አሁንም ችግሮች እየባሱ ነው የሚሄዱት። ዋግ በርካታ የመልማት አማራጭ አለው፤ ነገር ግን እየለማ አይደለም። የዓሳ ሀብት፣ የማር ምርት፣ የማዕድን አማራጭ አለ። ነገር ግን ትኩረት አልተሰጠም። ዋግን ከእርዳታ ለማላቀቅ ልማቶችን መሥራት ይገባል።
የዋግ ሕዝብ በመሠረተ ልማት ችግር እየፈተነ ነው።
በወረራ ያሉ ንጹሐንን እንድረስላቸው ስቃይ ውስጥ ነው ያሉት።
ክልሉ የተሸከመው የሀገር ጦርነት ነው። የተወረሩ አካባቢዎች የተሸከሙት የክልሉንና የሀገር ችግር ነው። የፌዴራል መንግሥት በጀት መድቦ መልሶ ሊያቋቁማቸው ይገባል።
የክልሉ ሕዝብ በኑሮ ውድነት እየተፈተነ ነው። መፍትሔ ልንሰጠው ይገባል።
የአማራ ክልል ለኢንቨስትመንት ምቹ እንዲሆን አሳሪ አሠራሮች አሉ። አገልግሎት አሰጣጣችን የተመቻቸ አይደለም። በኢንቨስትመንት የተሻለ ክልል ለመፍጠር ብልሹ አሠራርን ማስቀረት ይገባል።
ለተማሪዎች የትምህርት ማካካሻ መሰጠት አለበት። እንደዚያ ካልሆነ በጦርነት የተጎዳውን ሕዝብ ተወዳዳሪ ማድረግ አይቻልም።
የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው ጉዳይ አቋም መያዝ ይገባል። በሀገራዊ ምክክሩ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች እልባት እንዲያገኙ ክልሉ ምን ያክል እየተዘገጀ ነው።
የአማራ ሕዝብ ከፍተኛ አደጋ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ተጋርጦበታል። አብዛኛው አካባቢዎች ነፃ ቢወጡም እንዴትና ለምን ተወረርን ብሎ መጠየቅ ይገባል። ከዚህ ትምህርት ካልወሰድን ለዳግም ወረራ እንጋለጣለን። ጠላት አሁን በመቶዎች እና በሚሊዮን በሚቆጠር የሰው ኀይል እየተዘጋጀ እያለ ካልተዘጋጀን ለዳግም ወረራ እንጋለጣለን፤ ይህም ሕዝባችን ዳግም ይጎዳል። ለሕዝባችን እውነቱን እየነገርን ለዳግም ወረራ እንዳይጋለጥ ማድረግ አለብን፤ ምክር ቤቱም ውሳኔ ያሳልፍ።
የአማራ ሕዝብ ከምንጊዜውም በላይ ለጥቃት ተጋላጭ ሆኗል፤ ቀጥተኛ ጥቃት እየተደረገበት ነው፣ በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ይህ እየሆነ ነው፤ በጅምላ እየተገደሉ እየተቀበሩ ነው። የሚወለዱ ሕፃናት አማራ እንዳይሆኑ ከእናታቸው ሆድ እየተወጡ እየተገደሉ ነው። ይህ ስቃይ መች ነው የሚቆመው።
አማራ በመሆን ብቻ የሚደርስ ጥቃት እንዲቆም ምክር ቤቱ ውሳኔው ማሳለፍ አለበት።
የተዛባ የኢኮኖሚ ድልድይ አለ ይህ መስተካከል ይኖርበታል።
በታርቆ ክንዴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/