“ኹላችንም የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል፤ ሰላም እናምጣ በሚል ሐሳብ መትጋት ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነን”የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

109

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሰላም እናቶች ጋር የትውውቅ፣ የጸሎትና የምርቃት መርኃግብር እያካሄደ ነው።
በመርኃግብሩ ላይ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ”ሀገራችን በብዙ ረሃብ ውስጥ ናት፤ የሰላም፣ የምግብ፣ መጠጥ ረሃብ ውስጥ ናት፤ መደማመጥና ፍትሕ ተርባና ተጠምታ ነው ያለችው” ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያን ረሃብ መፍታት የሚቻለው መነጋገር መመካከር መደማመጥ ሲቻል ብቻ መኾኑን ገልጸዋል።
የእናትና አባቶቻችን በጎ ሐሳቦች ቢደመጡ ኖሮ ሙሾ ባላወረድን ነበር ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን “ኢትዮጵያ ለሁላችን እኩል እናት መሆን አለባት፤ ለዚህ ደግሞ ተነጋግረን እና ችግሮችን መፍታት ስንችል ወደ ሰላም፣ እርቅ እና እኩልነት እንመጣለን ብለዋል።

“ኹላችንም የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል፤ ሰላም እናምጣ በሚል ሐሳብ መትጋት ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነን” ነው ያሉት።
“ብዙ ሽህ ዓመታት ባስቆጠረው የሀገራችን የውይይት ምክክር፣ እርቅ፣ ልምድና የውጭውን ሁኔታ በማካተት ኮሚሽኑ ሲሠራ ውጤታማ እንደሚኾን ያምናልና ኹላችሁም ለውጤቱ አግዙን”ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ- ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የ134 ሚሊዮን ብር በላይ ሰብዓዊ ድጋፍ እና የመልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት አስጀመረች፡፡
Next articleለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የፌዴራል መንግሥት በጀት እንዲመድብ የምክር ቤት አባላት ጠየቁ።