
አዲስ አበባ፡ መጋቢት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በጸጥታ ችግር እና በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚቀርብ የ134 ሚሊዮን ብር በላይ ሰብዓዊ ድጋፍ እና የመልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት አስጀመረች፡፡
ዛሬ በይፋ የተጀመረው ፕሮጀክት በአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች ጉዳት ለደረሰባቸውና የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ እና መልሶ ለማቋቋም የሚውል መኾኑን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ እ.ኤ.አ በ2022 ተግባራዊ እንዲሆን አቅጣጫ ያስቀመጠበት የሰብዓዊ ድጋፍ አካል የኾነው ይህ ፕሮጀክት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያኒቱ ከምታከናውናቸው ማኅበራዊ ልማቶች አንዱ አካል መኾኑ ተገልጿል፡፡
ቤተክርስቲያኒቱ 134 ሚሊየን 884 ሺህ 285 ብር በመመደብ ለ227 ሺህ 255 ወገኖች የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን ታደርሳለች ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ የሚከናወነው በቤተክርስቲያኒቱ የልማት ኮሚሽን ሀገረ ስብከቶች አማካኝነት በተጠቀሱት አራት ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 7 ዞኖችና 11 ወረዳዎች መኾኑን በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሓፊ ዶክተር አባ ተሾመ ፍቅሬ ተናግረዋል፡፡
ቤተክርስቲያኒቱ በጤና፣ በትምህርት፣ በምግብ ዋስትና፣ በሴቶች የኢኮኖሚ እድገት፣ በንጹሕ መጠጥ ውኃ፣ በስደት እና ከስደት ተመላሾች ፕሮጀክቶች እንዲሁም በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ በ194 ፕሮጀክቶች 7 ሚሊዮን ሕዝብ ተጠቃሚ ማድረጓን በፕሮጀክት ማስጀመሪያ እና እየተካሄደ ባለው የጳጳሳት ጉባኤ ተገልጿል፡፡
ዘጋቢ፡- ድልነሳ መንግሥቴ – ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/