
መጋቢት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገራዊ ዲፕሎማሲ የቅንጅት መድረክ ውይይት መርኃግብር እያካሄደ ነው።
ከተመሰረተ 10 ዓመታት ያስቆጠረ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የቅንጅት መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ የተለያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ የፋይናንስ ተቋማትና ጉምሩክን ጨምሮ በርካታ የፌዴራል ተቋማትን በአባልነት ያቀፈ አደረጃጀት ነው።
በዛሬው መድረክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሬድዋን ሁሴን እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በውይይቱ ዓለምአቀፋዊና ውስጣዊ ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ የተሻለ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲኖር ችግሮች መለየትና መፍታት ላይ ያለመ ነው።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የንግድ ሚዛኑን ለማመጣጠን ተጨማሪ የወጪ ምርቶችን ማምረት፣ ከውጭ ገቢ ተኪ ምርቶች ላይ ማተኮር እና የውጭ ምንዛሬ ግኝት የሚያስገኙ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ላይ ትኩረት ታደርጋለች ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ በመሠረተ ልማት ዝርጋታና በኢንቨስትመንት አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻልና ማበረታቻዎችን በመተግበር ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት የንግድ ሚዛንን ማስጠበቅ ይገባል ነው ያሉት።
በተለያዩ ክፍላተ ዓለማት የሚገኙ የዲፕሎማሲ ተቋማትም ከፖለቲካ ዲፕሎማሲ ባሻገር ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉዳይ የዕለት ሥራችን መኾን አለበት ብለዋል። ይህን ለማሳለጥ ኹሉም አካላት (የግልና የመንግሥት ባለድርሻዎች) ተቀራርቦ መነጋገር አለብን፤ በብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ትኩረት የተደረገባቸው የአርብቶ አደር አካባቢዎችን ፀጋዎች ወደ ኢንቨስትመንት የመለወጥ ውሳኔዎችን ለመተግበር እንደሚሠራም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ተግዳሮቶችን ለመፍታትና የፖሊሲ ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችንን መልክ ለማስያዝ መድረኩ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/