የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡ በጉባኤው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላት ያነሷቸው ጥያቄዎችና ሐሳቦች:

195

ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
👉የምክር ቤት አባላቱ የፀጥታ፣ የመልካም አሥተዳደርና የዘላቂ ሰላም ጥያቄዎችን አንስተዋል።
👉በሌሎች ክልሎች ያሉ አማራዎች ሰቆቃ የሚያበቃው መቼ ነው?
👉ለጦርነቱ የተሰበሰበው በጀትና የወጣው ወጪ በኦዲት ሪፖርት መቅረብ አለበት።
👉በምሥራቅ አማራ ያሉ ተፈናቃዮች ጉዳይ በትኩረት መታየት እንደሚገባው።
👉ከሥራ አጥነት እና የኑሮ ውድነት በኩል ግልፅ የሆነ ሪፖርት አልቀረበም።
👉በክልሉ ወጣቶች በከፍተኛ ደረጃ የሥራ አጥነት ችግር አለ።
👉ወጣቶችን የሥራ እድል ለመፍጠር ከታሰበው ከ10 በመቶ በታች ነው የተሳካው በዚህ ላይ በትኩረት መሠራት ይኖርበታል።
👉የንፁህ መጠጥ ውኃ ግንባታ ፕሮጀክት በዝቅተኛ ደረጃ ነው፣ ትኩረት ቢሰጠው።
👉በሺዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸው፣ መምህራን ለዘመቻ ወጥተው በነበረበት ሂደት በትምህርት ሚኒስቴር የተሠጠው ምላሽ ችግሩን ችላ ያለ ነው። የክልሉ መንግሥት ተገቢውን ጥናት ማድረግና ችግሩን መፍታት አለበት።
👉ማኅበረሰቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢ በሆነ መንገድ ቢመለሱ።
👉ሙስና እና ብልሹ አሠራርን በመዋጋት አጥፊዎችን መቅጣት ፣ በእውነት የሚሠሩትን ደግሞ መሸለም የሚቻልበት ሂደት ቢኖር።
👉በአማራ ክልል ላይ ሲሠራ ከቆየው የተሳሳተ ትርክት፣ የወሰንና የማንነት ጥያቄ፣ ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ አማራዎች ስቃይና ሌሎች ጉዳዮች በብሔራዊ ምክክር መድረኩ መፍትሔ እንዲያገኙ ይሠራ
👉የሽብር ቡድኑ አሁንም ለድጋሜ ወረራ እየተንቀሳቀሰ ነው፣ ትጥቅም እያገኘ እንደሆነ መረጃ እየወጣ ነው፣ ይህ ክልል ድጋሜ እንዳይወረር ምን እየተሠራ ነው።
👉የአሜሪካ መንግሥት እያደረገው ባለለው የኤች አር 6600 ውሳኔ ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ቢያሳልፍ።
👉የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በትኩረት መሠራት አለበት። መልሶ ለማቋቋም ደግሞ መላው ኢትዮጵያን ቢነሱ፣ ይህ ሲሆን ወንድማማችነት ይጠናክራል፣ ዜጎችም በቶሎ ይቋቋማሉ። በትንንሽ ሥራ ብቻ ዜጎችን ማቋቋም ስለማይቻል ታላላቅ እቅዶች መታቀድና እና በትኩረት መሥራት ይገባል።
👉ድህነትን ለመቅረፍ ግብርና ላይ በትኩረት መሠራት አለበት። የሚቀጥለው የምርት ዘመን ምን ሊሠራ እንደታሰበ በሪፖርቱ አልቀረበም። የማዳበሪያ እጥረት እንደሚከሰት ይጠበቃል ይህ ቢሆን ምንድን ነው የምናደርገው የሚለውን ከአሁኑ ማሰብ ያስፈልጋል።
👉አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር አለ፣ ባለሙያዎች እና መሪዎች ቅንነት ይጎድላቸዋል፣ ይሄን ማስተካከል ያስፈልጋል።
👉በክልሉ ያሉ የልማት ድርጅቶች ስም ባልተገባ መንገድ ስማቸው ሲጠፋ የክልሉ መንግሥት ለጉዳዩ ምላሽ ለምን አልሰጠም።
👉ክልሉ ከሌሎች ክልሎች ጋር አብሮ እንዳይሠራ የሚደረግ ዘመቻ አለ፤ የክልሉ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ምን ለመሥራት አስቧል።
👉ተከፋይ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂ ነኝ ባዮች ክልሉ እንዲከፋፈል፣ መሪዎች እንዲከፋፈሉ እያደረጉ ነው፣ ይህ ቡድን ሃይ ሊባል ይገባል። እነዚህ ከፋፋዮች ሕዝቡ እንዳይሰማቸው ማድረግ መቻል አለበት። ጠበቅ ያለ ሥራ መሠራት ግድ ይላል። የክልሉ የኮምዩኒኬሽን ቢሮ በጉዳዩ ላይ የሚሠራውን ሥራ በግልጽ ማሳየት አለበት። በከፋፋይ ተከፋይ አንቂ ነን ባዮች ምክር ቤቱ ተወያይቶ ግልጽ የሆነ አቋም መውሰድ አለበት።
👉በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ወረዳዎች የመንገድ ችግር በመኖሩ እና ችግር ሲፈጠር ቶሎ መድረስ ስለማይችል ለኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን ምሽግ እንዲሆን እያደረገ ነው፣ መፍትሔ ይሰጠው።
በታርቆ ክንዴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአሸባሪውን የትግራይ ቡድን የዳግም ወረራ ዝግጅት ለመቀልበስ ጠንካራ የውስጥ ዝግጅት ማድረግ እና አንድነትን መጠበቅ እንደሚገባ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡
Next articleየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገራዊ ዲፕሎማሲ የቅንጅት መድረክ ውይይት መርኃግብር እያካሄደ ነው።