
ባሕር ዳር: መጋቢት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በምክር ቤቱ የ2014 በጀት ዓመት የክልሉን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ ካስተላለፏቸው መልዕክቶች
•የአሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ ለመቀልበስ መስዋእትነት ለከፈሉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ በራሳቸው እና በክልሉ ምክር ቤት ስም ያላቸውን አድናቆትና አክብሮት ገልጸዋል።
•የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ምዕራፍ የኾነውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት በመጀመሩ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል
•የአሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ ለመመከትና ለመቀልበስ የክልሉ መንግሥት ሙሉ ትኩረቱን በማድረግ በኅልውና ዘመቻው መላ ሕዝቡን የማነቃነቅ ሥራ ሠርቷል ብለዋል።
•የክልሉ መንግሥት ያደረገውን የክተት ጥሪ በመቀበል ሕዝቡ፣ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ ተጋድሎ እንዳደረገም ገልጸዋል።
•በአንድነት ኀይል የተከናወነው የኅልውና ዘመቻ ወረራውን ለመቀልበስ በርካታ ውጤቶችን እንዳስገኘም ጠቅሰዋል።
•በጋራ ጉዳዮች ላይ ተባብሮና ተቀናጅቶ በመሠራቱ የኅልውና ዘመቻውን ለማሳካት ወሳኝ አስተዋጽኦ አድርጓል፤ ይህም ለሰላምና ለልማት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
•እንደ ክልል እና እንደ ሀገር ወራሪ ቡድኑ ያደረሰውን ጉዳት እና ውድመት ለውጭ ሚዲያ አካላት ማስገንዘብም ኾነ የሽብር ቡድኑን ማንነት በሚፈለገው ልክ እንዲታወቅ ማድረግ በታቀደና በተደራጀ መንገድ መሠራት አለበት ነው ያሉት።
•በሕዝቦች መካከል ልዩነቶችን የሚያሰፉና አንድነትን የሚጎዱ አሉባልታ ወሬዎችን የክፋት ንግግሮችን ሕዝቡ በንቃት እንዲከታተልና እንዲያወግዝ የሚያስችል ተከታታይነት ያለው የኮምዩኒኬሽን ሥራ ማከናወን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
•የክልሉን ሰላምና ደኅንነት ለመጠበቅና ከጥቃት መከላከል የሚያስችል የኀይል ግንባታ ተግባር በአግባቡ ታቅዶ በተቀናጀ መልኩ እየተሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል።
•ወጣቱ በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በአማራ ልዩ ኀይል በመቀላቀል እንደስካሁኑ የወራሪ ቡድኑን ቅስም ለመጨረሻ ጊዜ በመስበር የተጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዘጋቢ:–በፍቃዱ አበበ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/