”ኤችአር 6600 ከፀደቀ የኢትዮጵያና የአሜሪካን ግንኙነት የሚሽር ነው” ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

280

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ የኤች አር 6600 ፍላጎት እስካሁን በኢትዮጵያ የተሠሩ መልካም ተግባራትን ኹሉ የሚክድና የሚሸረሽር ነው ብለዋል።
በሳምንቱ ከኤች አር 6600ና ኤስ 3199 የተባሉ አደገኛ ረቂቅ ሕጎች እንዳይጸድቁ ዳያስፖራው በተቀናጀ የአንደነት ዘመቻ እንዲንቀሳቀስ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡
ዳያስፖራው በኢትዮጵያ የውጭ ጣልቃ ገብነት በበቃ ወይም No more ዘመቻ እንዳከናወነ ኹሉ ኤች አር 6600ና ኤስ 3199 የተባሉ አደገኛ ረቂቅ ሕጎች መመከት እንዲችሉ ተወያይተዋል ብለዋል።
በፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር የኹለትዮሽ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል፡፡
“ከዒድ እስከ ዒድ” ታላቁ ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ መርኃግብር የተሳካ እንዲኾን በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ – ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleኢትዮ ቴሌኮም አዲስ 4ጂ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለመኖሪያ ቤት አቀረበ።
Next article“የክልሉን ሰላምና ደኅንነት ለመጠበቅና ከጥቃት መከላከል የሚያስችል የኀይል ግንባታ ተግባር በአግባቡ ታቅዶ በተቀናጀ መልኩ እየተሠራ ነው” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)