
መጋቢት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም መደበኛ ኢንተርኔት ተደራሽ ባለኾነባቸው የቦታዎች ላይ በአማራጭነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል 4ጂ ገመድ አልባ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለመኖሪያ ቤት ማቅረቡን ገልጸዋል።
አገልግሎቱ ደንበኞች በመኖሪያ አካባቢያቸው 4ጂ የሞባይል ኔትወርክን በመጠቀም ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ በቤት ውስጥ ማግኘት የሚያስችል አማራጭ ነው ተብሏል።
በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ የሽያጭ ማዕከሎች ከአገልግሎት መስጫ ቀፎ ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መጀመሩን ገልጿል።
የፊክስድ ብሮድባንድ በመኖሪያ ቤት እና በንግድ ተቋማት ባለበት እንደሚቀጥል የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።
በአግልግሎቱ 70 ሺህ ደንበኞች በአጭር ጊዜ ለማፍራት ታቅዷል።
በኢትዮጵያ 136 ከተሞች የአራተኛውን ትውልድ (4G) አገልግሎት ተጠቃሚዎች ናቸው ተብሏል ።
ዘጋቢ:- ዳንኤል መላኩ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/