
መጋቢት 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በሁለትዮሽ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
አሸባሪው ሕወሓት በአጎራባች ክልሎች ላይ እያደረሰ ባለው ትንኮሳ ምክንያት የሰብዓዊ ርዳታ ፍሰቱ ላይ እንቅፋት መፍጠሩን ገልጸዋል።
“ኤች. አር 6600 እና ኤስ 3199 የተሰኙ ረቂቅ ሕጎች የሁለቱን ሀገራት የቆየ እና ታሪካዊ ግንኙነት የማያንፀባርቁ ናቸው” ብለዋል።
ረቂቅ ሕጎቹ በሀገሪቱ ሰላምና ዲሞክራሲን ከማስፈን ይልቅ የኢትዮጵያውያንን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ መኾኑን በመገንዘብ በአሜሪካ በኩል ውድቅ ሊደረጉ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የወሰዳቸውን አበረታች የሰላም እርምጃዎችን አስመልክተውም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የወሰዳቸውን አወንታዊ እርምጃዎችን በተመለከተ ሀገራቸው በአድናቆት የምትመለከተው እና እውቅናም የምትሰጠው መኾኑን መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/