“መንግሥት ሰላምና ደኅንነታችን ሊያስከብርልን ይገባል” የምዕራብ ጎንደር ዞን ነዋሪዎች

152

ገንዳ ውኃ: መጋቢት 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ “የፈተናዎች መብዛት ከብልጽግና ጉዟችን አያስቆመንም” በሚል መሪ ሐሳብ በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይት አድርጓል።
ገዥው ፓርቲ በድርጅታዊ ጉባኤው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚመለከት ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎችም መንግሥት ሰላምና ደኅንነታቸውን እንዲያስከብርላቸው ጠይቀዋል።
ከመተማ ጎንደር የሚወስደው መስመር በሕገ ወጥ መንገድ በተደራጁ ሽፍቶችና የገንዘብ ጥመኞች በመከበቡ ዜጎች በነጻነት እንዳይንቀሳቀሱ፣ እንዲታገቱና እንዲሞቱ እየተደረገ መሆኑን ነው ተሳታፊዎች የተናገሩት።
በዞኑ ጫካና ሕዝብን ተገን አድርገው የተደራጁ ሕገ ወጥ ወንጀለኞች ለደኅንነታቸው እንዳሰጋቸው የገለጹት ተሳታፊዎቹ መንግሥት ወንጀለኞችን በሕግ ቁጥጥር ሥር አውሎ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ብለዋል።
በዞኑ እየተፈጸመ ስላለው የሰዎች እገታና ሞት ባሻገር በሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ያለውን የመድኃኒት እጥረት፣ የውኃና የመብራት ችግሮች፣ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን እንዲሁም የ12ኛ ክፍል የተማሪዎችን ውጤት በተመለከተ መንግስት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥባቸውም ተሳታፊዎች ጠይቀዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢክስ ወርቄ ፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት በመፍጠርና የጸጥታ መዋቅሩን በማደራጀት የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ሢሠራ መቆየቱን ገልጸዋል። በቀጣይም የጠላት ኃይል ለአካባቢው ስጋት በማይሆንበት ደረጃ ትግላችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
በውይይቱ የተገኙት የሰቲት ሑመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አሸተ ደምለው በበኩላቸው በህገወጥ መንገድ ሰዎችን የሚያግቱና የሚገሉ ወንጀለኞች የወጡት ከሕብረተሰቡ ነውና ሕገወጥ እገታና ግድያን የሚፈጽሙ ወንጀለኞችን ሕብረተሰቡ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት በጋራ ሊዋጋ ይገባን ብለዋል።
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት በትክክል እንዲታይ ክትትላችን አጠናክረን እንቀጥላለንም ነው ያሉት አቶ አሸተ።
በዞኑ እየተስተዋሉ ያሉ የሰላምና ደኅንነት ስጋቶች መንግሥት የቀጣይ ዕቅድ አካል አድርጎ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ የተናገሩት ደግሞ የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ ናቸው።
አቶ ሲሳይ አክለውም በኢንቨስትመንት መሬት ተቀብለው ለታቀደለት ዓላማ በማያውሉ እና ወደ ልማት ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ መንግሥት ተገቢውን የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ ነው የገለጹት።
የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ይርጋ ሲሳይ በበኩላቸው መንግስት የሕብረተሰቡን ሰላምና ደኅንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ በዞኑ ባሉ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ወርዶ ይሠራል ብለዋል።
እንዳንከባበር እንዳንደጋገፍና አንድነት እንዳይኖረን የሚሠሩ ጠላተቶች በሕብረተሰቡ ውስጥ ተሰግስገው መኖራቸውን የተናገሩት አቶ ይርጋ የተደራጀ ግድያን፣ ጠለፋና እገታን እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ ትንኮሳዎችን ለማስቆም ከሕብረተሰቡ ጋር በጋራ እንሠራለን ብለዋል።
ዘጋቢ:–ቴዎድሮስ ደሴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በቻይና ኢስተርን አየር መንገድ በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡
Next article“ጦርነቱ እና የጸጥታ መደፍረሱ በተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ የሚታወቅ ኾኖ ሳለ ትምህርት ሚኒስቴር ጉዳዩ በአግባቡ ሳይታይና ሳይፈተሸ በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አወሳሰን ላይ የሚታይ ነገር የለም ማለቱ ተገቢ ውሳኔ አይደለም” የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም