
መጋቢት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ተላላኪው ኦነግ ሸኔ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ካደረሱባቸው አንዱ ነው የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳዳሪ አሕመድ አሊ ለአሚኮ እንዳሉት በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሽብር ቡድኖቹ በርካታ ንጹሐን ወገኖችን ጨፍጭፈዋል፡፡ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመንግሥትና የግለሰቦችን ንብረት ወድሟል፤ ተዘርፏል፡፡ በሽብር ቡድኖቹ በርካታ ወገኖች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ሴቶች ተደፍረዋል፤ ከ282 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ደግሞ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው እንደነበር አስገንዝበዋል።
በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና እና በንጹሕ ውኃ ተቋማት ላይ የደረሰው ውድመት ማኅበረሰቡን ለከፍተኛ ችግር መዳረጉንም ገልጸዋል፡፡ ተቋማቱን በፍጥነት መልሶ ለመገንባት ዓላማ ያደረገ የምክክር መድረክ መጋቢት 18/2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድም አስታውቀዋል።
አቶ አሕመድ በመድረኩ ከ250 በላይ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ተወላጆችና አጋር ባለሃብቶች፣ ዳያስፖራዎች፣ አማራ ልማት ማኅበር (አልማ)፣ ልማታዊ ድርጅቶች፣ የክልልና የፌዴራል የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃልም ብለዋል።
በምክክር መድረኩ ስለብሔረሰብ አሥተዳደሩ አጠቃላይ የመልሶ ግንባታ፣ የሰላምና ልማት ተግባራቶች ዙሪያ በሰፊው እንደሚመከርበት ተጠቅሷል፡፡
ዘጋቢ:- ሥነ-ጊዮርጊስ ከበደ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/