
ሰቆጣ: መጋቢት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር እናቶች እና ሕጻናት ለከፋ ርሃብ ተጋልጠዋል። በብሔረሰብ አስተዳደሩ ዝቋላ ወረዳ ጽጽቃ ጤና አጠባበቅ ጣብያ
ሕጻናት የማገገሚያ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
ሙሉነሽ መለሰ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዝቋላ ወረዳ ቀበሌ 06 ነዋሪ ናቸው። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በቀበሌው በፈጸመው ወረራ ሀብትና ንብረት በመዝረፉ እና የሕጻናት አልሚ ምግብ በመውደሙ የሚቀመስ ምግብ የለም።
በዚህ ጊዜ ነበር እናት ልጃቸውን ይዘው ወደ ዝቋላ የስደተኞች መጠለያ ጣብያ የተቀላቀሉት። በዚህ መጠለያ ጣብያ ምግብ ማግኘት ባለመቻሉም ሕጻናት ለከፋ ርሃብ ተጋልጠዋል።
በማገገሚያው የሚገኙ ሕጻናትን እንደተመለከትነው የሕጻናቱ የሰውነት መገጣጠሚያ ታጥፎ ለመዘርጋት አዳጋች ኾኗል፤ ያለመረጋጋት እና ያለማቋረጥ የሲቃ ድምጽም ይሰማል። የሕጻናት ቆዳቸው ተሸብሽቦ፣ አጥንታቸው ብቻ ቀርቷል።
ከወረዳው ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በዝቋላ ወረዳ 661 ሕጻናት መካከለኛ፣ 381 ሕጻናት ደግሞ ከፍተኛ የሥነ ምግብ ችግር አጋጥሟቸዋል። 899 እናቶችም በተመሳሳይ ለምግብ ችግር ተጋልጠዋል።
አራት ጤና ጣብያዎች፣ አንድ ሆስፒታል እና ዘጠኝ ጤና ኬላዎች ተዘርፈዋል። እነዚህ ተቋማት 75 በመቶ ለሚኾነው የወረዳው ሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ነበሩ።
በዝቋላ ወረዳ ከሚገኙ 15 ቀበሌዎች 6 ቀበሌዎች አኹንም በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሥር ይገኛሉ።
ዘጋቢ:–ዳግማዊ ተሠራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/